ስስታሙ ውሻ
በዛርኬ ጎይቴ የተተረከ
አንዲት ውሻ በአንድ ወቅት ወደ አንድ ታዋቂና ያረጀ ውሻ የቀብር ስነ ስርአት ላይ ተገኝታ ያየችውን ትልቅ የስጋ ጉማጅ መንትፋ በመውጣት “ይህንን ጥሩ ስጋ ከልጄ ጋር ነው መብላት ያለብኝ፡፡” በማለት በፍጥነት ስጋውን ይዛ በሰላም ወደቤቷ ለማድረስ ሮጠች፡፡ ሆኖም ከቤቷ አቅራቢያ ካለው አንድ ኩሬ ዘንድ ደርሳ ልትሻገር ስትል አቆልቁላ ስትመለከት በአፏ የያዘችውን ስጋ ምስል ውሃው ውስጥ ተመለከተች፡፡ ስጋውም በአፏ ውስጥ ከያዘችው ስጋ ገዝፎ ስለታያት ውሃው ውስጥ ያየችውን ትልቅ ስጋ ለመውሰድ በመፈለግ አፏን ስትከፍት ይዛው የነበረው ስጋ ውሃው ውስጥ ወድቆ ጠፋ፡፡ ሆኖም ውሻዋ አሁንም ውሃው ውስጥ ያየችውን ስጋ ለመያዝ ብትሞክርም ስላልቻለች በፀፀት እያለቀሰች የያዘችውን ስጋ አጥታ ወደቤቷ ተመለሰች፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|