ባህላዊ አኗኗር
በቻሜ ክዌር የተተረከ
ከአመታት በፊት ሰዎች ወንድና ሴት ሆነው በቤተሰብ ውስጥ አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ ወንዶቹ ከቤት ውጪ ሲኖሩ ሴቶቹ እቤት ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ ሴቶቹ ምግብ አብስለው ለወንዶቹ ሲወስዱላቸውና አቅራቢያቸው ሲደርሱ በተወሰነ ርቀት ያህል በጉልበታቸው ተንበርክከው በመሄድ ምግቡን ከፊታቸው ያስቀምጣሉ፡፡ ምግቡንም ካስቀመጡ በኋላ ሲሄዱ ወንዶቹ መመገብ ይጀምራሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወንዶቹ ከተመገቡ በኋላ ሴቶቹ ተመልሰው ወይም ከወንዶቹ ጋር የሚኖሩት ወንድ ልጆች የበሉበትን እቃ ይወስዳሉ፡፡ ይህ ባህላዊ አኗኗራቸው ነበር፡፡
በመንደሩ ውስጥ ያሉ ሰዎች በጨዋታና በጭፈራ ላይ ይተዋወቃሉ፡፡ ወንድ ልጆችና ልጃገረዶች፣ አዋቂ ወንዶችና ሴቶች በመንደሩ አቅራቢያ ወደሚገኝና የአካባቢው አለቃ በባለቤትነት ወደ ያዘው ሰፊና ግልፅ የጨዋታ ቦታ ይሄዳሉ፡፡(አብዛኛውን ጊዜ ለመንደሩ አለቆች ክብር ሲባል መሄድ አይቻልም ነበር፡፡)
ራሳቸውንም ከጥቃት ለመከላከል መሳሪያ ይይዙ ነበር፡፡
በቀድሞ ጊዜ ባልና ሚስት አብረው አይበሉም ነበር፡፡ አሁን ግን ይህ ተቀይሯል፡፡ ባልና ሚስት በአንድ መአድ ይመገባሉ፤ ወንድና ሴቶችም አብረው ተቀምጠው በጋራ ይመገባሉ፡፡
የአኝዋክ ባህል በማክበር ላይ የተመሰረተ ሲሆን ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ለወንዶች ዘመዶቻቸው እቃ የሚያመጡ ልጃገረዶችም ወንዶች አጠገብ የሚቀርቡት ተንበርክከው ነው፡፡ ይህ ከአመታት በፊት ይፈፀም ነበር፡፡ አሁን ግን ይህ አይደረግም፡፡ አዲሱ ትውልድ ይህንን ሊያውቅ ይገባል፡፡
(የዚህ ታሪክ ተራኪ ዘመናዊውን ባህሪ ይኮንናል፡፡) ክብር ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም ወንድ የሚፈልገውን ማግኘት ይችላልና፡፡ በአሁኑ ዘመን ልጆች ወላጆቻቸውን አያከብሩም፡፡ ወንድና ሴት ልጆች ሲጠሩ መጥተው ሳይንበረከኩ አባታቸው ፊት ይቆማሉ፡፡ ልጅ ሲጠራና ሲመጣ ወይም ስትመጣ መጀመሪያ አቤት ማለት አለባቸው፡፡ አሁን ግን ለአባታቸው መልስ እንኳን አይሰጡም፡፡ ባህላዊ የክብር ዋጋ ጠፍቷል፡፡ የድሮ አኗኗር መረሳት የለበትም፡፡
ድሮ ቅደመ አያቶቻችን የእንስሳት ቆዳ ይለብሱ ነበር፡፡ በኋላ አንዳንዶች ልብስ መልበስ ጀመሩ፡፡ ይህ ጥሩ አይደለም፡፡ ሰዎች በመንደር ተሰባስበው በመኖር ጠላቶቻቸውን በጋራ ይከላከሉ ነበር፡፡ ከብረት የተሰራ ሳይሆን ከተጠረበ እንጨት የተሰራ አዲያንግ የተባለ የጦር መሣሪያ ነበራቸው፡፡ በጦርነት ወቅት ከጉማሬ ቆዳ የተሰራና ጦር የማይበሳው አዌንግ የተባለ ጋሻ ይጠቀሙ ነበር፡፡ አሁን ከብረት የተሰሩ መሳሪያዎችና ጠመንጃዎች ከመጡ ወዲህ ሰዎች ጦርነት አይገጥሙም ምክንያቱም እንገዳደላለን ብለው ይፈራሉ፡፡ በፊት የሚሞቱት ወይም የሚቆስሉት አንድ ወይም ሁለት ብቻ ሲሆኑ አሁን ግን ብዙ ሰዎች ሊገደሉ ይችላሉ፡፡
የበቀል ግድያዎችም ነበሩ፡፡ ገዳዩም ተይዞ ይገደል ነበር፡፡ አሁን ግን ከጃንሆይ ውድቀት ወዲህ ይህ ሙሉ ለሙሉ ቆሟል፡፡ ወንጀሉን ያልፈፀመ ሰው ሊያዝ ቢችልም ሳይገደል ለሟች ካሳ እስኪከፈል ድረስ በቁጥጥር ስር ይውል ነበር፡፡ ይህ ግን በእውነቱ መጥፎ ድርጊት ነው፡፡ በዚህ መልኩ በቀልን መወጣት ሲጀመር ብዙ ነገር ተባዛ፡፡ ማንም ሰው ከመንደሩ ተይዞ ሊወርድ ይችላል፡፡ ሰው ሲገደል ጉዳዩን ያቀለው ነበር፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|