ነፍሰ ጡሯ ሴትና አንበሶች
በአክዋይ ኦጁሉ የተተረከ
በአንድ ወቅት አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት ነበረች፡፡ ይህችም ሴት የምትኖርበትን ቦታ ፍለጋ በመዞር ላይ ሳለች ወደ አንድ የአንበሣ ጉድጓድ ዘንድ ትደርሳለች፡፡ አንበሳው ጉድጓድ ውስጥም ስትገባ ልጅ ትወልድና አንበሶቹ ይመግቧት ጀመር፡፡ የምትመገብበትንም ማንኪያ ቢሰጧትም ሾርባው ከማንኪያው ላይ እየፈሰሰ ህፃኑን ስላስለቀሰው አንበሶቹ የህፃኑ ጩኸት አፍዝ አደንግዝ ነው ብለው ስለፈሩ ገብሳቸውን፣ ባቄላቸውንና፣ ሁሉንም ነገር ጥለው ስለሸሹ ሴትየዋ የአንበሶቹን ንብረት ወረሰች፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|