የሚያንጋጥጠው ጅብ
በኦኮክ አጁሎ የተተረከ
በአንድ ወቅት የአንድ መንደር ወንዶች ወደ አደን ሄዱ፡፡ የዱር እንስሳትም ገድለው ወደቤት ይዘው የሚሄዱትን ሥጋ የሚደብቁበት ቦታ አዘጋጁ፡፡ አሞራዎችም በስፍራው ላይ እያንዣበቡ በቡድን ያልፉ ጀመር፡፡ በጭስ እየደረቀ ያለውንም ስጋ ጠረን እየተከተሉ ያንዣብቡ ጀመር፡፡
አንድ ጅብ የአሞራዎቹን አቅጣጫ በመመልከት ሥጋ ወዳለበት ቦታ እንደሚወስዱት ስለሚያውቅ ተከተላቸው፡፡ ነገር ግን ወደ አሞራዎቹ እያንጋጠጠና ጭሱን እየተከተለ ሲሄድ በድንገት ከሥፍራው ደርሶ እሳቱ አጠገብ በመጋጨት አንድ እግሩ ድስቱ ውስጥ ገባበት፡፡
እግሩም እየተቃጠለ መሆኑ ሲሰማው ሁሉም ብድግ ብለው ሲያዩት ጅቡ ደንግጦ ስለወደቀ ሰው ሁሉ ስቆበት ሌላ ጉዳት ሳይደርስበት ሮጦ ሄደ፡፡
የዚህ ተረት መልዕክት የምንሄድበትን እናስተውል፤ በጥንቃቄም እንጓዝ፤ አውሬ እንዳይበላንም ፊታችንን እንመልከት የሚል ነው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|