ስስታሙ ባል
በአኩችችዋች ቺቢ የተተረከ
በአንድ ወቅት ድርቅ ስለገባ ረሃብ ነበረ፡፡ አንድ የተረገመ ሰው ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር አብሮ ይኖር ነበር፡፡ በረሃቡም ጊዜ ወደ ጫካ ሄደው የሚበላ ነገር ፍለጋ ወጡ፡፡ በድንገት ሚስትየው የሞተ እንስሳ ከሩቅ አየች፡፡
በመቀጠልም “የሞተ እንስሳ አየሁ፡፡ እድለኛም ነኝ፡፡ እግዚአብሔር ለእኔና ለልጆቼ የሚበላ ነገር ሰጠን፡፡” አለች፡፡
ነገር ግን ባሏ የሞተው እንስሳ ጥሩ መሆኑን ሲያይ “እኔ ነኝ ቀድሜ ያየሁት፡፡” አለ፡፡
ወደ እንስሳውም በደረሱ ጊዜ ባልየው “ይህ ሁሉ የእኔ ነው፡፡ ምንም የምትበሉት ነገር አልሰጣችሁም፡፡” አላቸው፡፡
ሴትየዋም ልጆቿ የሚበሉት መራራ ፍሬ ይዛ መጥታ ውሃ ፍለጋ ሄደች፡፡
ሆኖም ውሃ አጥታ ስትማስን ቆይታ አንድ የውሃ ጉድጓድ አገኘች፡፡ ተመልሳ መጥታም አሁንም ሥጋውን እየገፈፈና እየቆራረጠ ለነበረው ባሏ ነገረችው፡፡
ወደ ጉድጓዱም የውሃ ቅል ይዛ ለመመለስ ብትፈልግም ባሏ እንዳትሄድ በመከልከል “እኔ ውሃውን ይዤ እመጣለሁ፡፡ ታዲያ እኔ ስሄድ ሥጋውን ለመብላት ትሞክሩና እቀጣችኋለሁ፡፡” አለ፡፡
የሥጋውንም ቁራጮች አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት፣ አራት እያለ ቆጠራቸው
“አንድ እንኳን ቢጎድል እቀጣችኋለሁ፡፡” አለ፡፡
ይህንን ያለው እሱ ቀድሞ መብላት ስለፈለገ ነው፡፡ ስለዚህ ሲሄድ ሚስቱን ማየት እንዲችል ወደኋላው መሄድ ጀመረ፡፡ ነገር ግን ጉድጓዱ ጋ ሲደርስ ስላላየው ከውስጡ ወድቆ ሲገባ አፈር ጨምረውበት ከቀበሩት በኋላ ሴትየዋ ከነልጆቿ ሥጋውን በሉት፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|