ዝንጀሮ፣ጦጣና ቀበሮ
በኦዶላ ኦዋር የተተረከ
ዝንጀሮ፣ ጦጣና ቀበሮ በአንድ አለቃ ቤት ይኖሩ ነበር፡፡ ሁልጊዜ አንድ ነገር እንዲያመጡ ሲላኩ ዝንጀሮውና ቀበሮው ከባዱን ሸክም ሲሸከሙ ጦጣው ግን ይህን አያደርግም ነበር፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ሶስቱም ለአለቃቸው አንድ ነገር ይዘው እንዲመጡ ሲላኩ እንደልማዳቸው ዝንጀሮውና ቀበሮው ከባድ ሸክም ሲሸከሙ ጦጣው ቀላል ሸክም ያዘ፡፡ ከጫካውም እንደደረሱ ዝንጀሮውና ቀበሮው ተንኮለኛውን ጦጣ እንዴት እንደሚገድሉት ተማከሩ፡፡ ወደ ቤትም በተመለሱ ጊዜ ቀበሮውና ዝንጀሮው ጦጣውን ወደኋላ በመተው ቀድመው ገብተው አለቃ አንበሣን እንዲህ አሉት “ጫማ ሳታደርግ ለምንድነው ሁልጊዜ በባዶ እግርህ የምትሄደው? በመንደሩ ያሉ ጫማዎች ሁሉ የሚሰሩት በጦጣው ስለሆነ ከሄደበት ሲመለስ ጠርተህ ጫማዎች እንዲሠራልህ ንገረው፡፡”
በዚህም መሠረት አለቃ አንበሣ ጦጣውን ጠርቶ “ጫማ አጥቼ እንዲህ ስሰቃይ እንዴት ዝም ትላለህ? በል አሁን ጫማ ሥፋልኝ::” አለው፡፡
ጦጣውም ጫማ መስፋት ስለማይችል በነገሩ ግራ ቢጋባም ይህንን መናገርና አለቃውን ማበሳጨት አልፈለገም፡፡
ከዚያም ጦጣው “ጫማ መስፋት እችላለሁ፡፡ ነገር ግን ጫማ የሚሰፋው ከዝንጀሮ ቆዳና ከቀበሮ አከርካሪ ነው፡፡” አለው፡፡
ስለዚህ ዝንጀሮና ቀበሮው ተገደሉ፡፡
ቆዳቸውም ከተገፈፈ በኋላ ለጦጣው ተሰጥቶት ውሃ ውስጥ ተነክሮ እንዲርስ ተደረገ፡፡ ጦጣውም ቆዳቸውን ወደ ጥልቁ ውሃ ከወረወረው በኋላ በውሃው ውስጥ የራሱን ምስል ስላየ ሶስት ቀን እዚያው ቆየ፡፡
ከዚያም አለቃው ጠርቶት “አሁን ቆዳዎቹ ስለለሰለሱ ጫማውን ለመስፋት ዝግጁ ናቸው፡፡” አለው፡፡
ጦጣውም ወደ ወንዙ ተመልሶ ሲሄድ የራሱን ምስል ውሃ ውስጥ እንደገና ሲያየው አንድ ሃሳብ መጣለት፡፡
ወደ አለቃው አንበሳም ሮጦ በመመለስ “ውሃው ውስጥ እንዳንተ ትልቅ አንበሣ አለ፤ ሊገድለኝም ይፈልጋል፡፡” አለው፡፡
አለቃው አንበሣም ቀበሮውን አስከትሎ ወደ ወንዙ ወረደ፡፡ ወንዙ አጠገብ እንደደረሱም ጦጣው ወደ ኋላ ቀረት ሲል አንበሣው የራሱን ምስል ውሃው ውስጥ ተመለከተ፡፡
አንበሣውም ሲያጓራ ምስሉም መልሶ አጓራበት፡፡ በዚህ ጊዜ አንበሣው ውሃው ውስጥ ያለውን አንበሣ ሊገጥም ዘሎ ገብቶ ሞተ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|