ጉማሬን ተኩሶ መግደል
በፒተር ኦቻንዴ የተተረከ
አንድ ቀን በንጉሱ ግቢ ውስጥ ጉማሬ ከውሃው ወጥቶ ሲገባ ያየ አንድ አቹር ኦጃላኮሮ የተባለ ሰው ለንጉሱ “አንድ ጥይት ቢሰጡኝ ጉማሬውን አይኑ ላይ መትቼ እገድለዋለሁ፡፡” አላቸው፡፡
ንጉሱም “አይሆንም አትሞክር፡፡” ቢሉትም አቹር በመጨረሻ አሳመናቸው፡፡
ጠመንጃና ጥይቱም ተሰጥቶት ጉማሬውን በአንዴ ተኩሶ አይኑ ላይ መትቶ ከገደለው በኋላ ሰዎቹን ገመድ ፈልገው እየጎተቱ ወደ ውሃው እንዲጥሉት አዘዘ፡፡ ሄደውም ጉማሬውን ባዩት ጊዜ እውነትም አይኑ ላይ ተመትቶ ነበር፡፡
“አላልኳችሁም!?” አለ አቹር “እንደማልስተው!”
ከዚያም ስጋውን ተከፋፍለው በሉት፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|