አይጥ አጥማጆቹ
በፒተር አቻንዴ የተተረከ
አንድ ካጋ የተባለ ልጅ ጓደኞቹን እንዲህ አላቸው “ሄደን አይጦችን እንያዝ፡፡” (ወጥመዱ የሚሰራው በተገመዱ ቅርንጫፎች ሲሆን ከስሩ ማጥመጃ ምግብ አለው፡፡ አይጡ የወጥመዱን ወስፈንጥር በተጫነው ጊዜ ተስፈንጥሮ ይይዘዋል፡፡)
ነገር ግን ልጁ ያዘጋጀው ወጥመድ ምግብም ሆነ ወስፈንጥር አልነበረውም፡፡
እሱም ጓደኞቹን እንዲህ አላቸው “ሄደን ወንዙ ውስጥ እንዋኝ፤ ወደ ውስጥም ጠልቀን እንግባ፡፡”
ጓደኞቹም ወንዝ ውስጥ እንዳሉ ካጋ ወደ ወጥመዶቹ ሮጦ በመመለስ የተያዙትን አይጦች በሙሉ ሰብስቦ ምግብም ሆነ ወስፈንጥር የሌለው የራሱ ወጥመድ ላይ ካስቀመጣቸው በኋላ ወደ ወንዙ ተመልሶ ከጓደኞቹ ጋር ጠልቆ ዋኘ፡፡
ከጥቂት ቆይታም በኋላ “አሁን ሄደን አይጦች ይዘን እንደሆነ እንመልከት፡፡” አላቸው፡፡
የሁሉም ወጥመዶች መዝጊያዎቻቸው የተዘጉም ቢሆን ከካጋ ወጥመድ በስተቀር አንዳቸውም አይጥ የለባቸውም ነበር፡፡
እርሱም “ካለ ምግብና ወስፈንጥር ምን ያህል አይጦች እንደያዝኩ ተመልከቱ፡፡ ምግብና ወስፈንጥር ባደርግበት ኖሮ ብዙ አይጦችን እይዝ ነበር፡፡” አላቸው፡፡
እነርሱም በሞኝነቱ ሳቁበት፡፡
ወደ ቤትም ሲመለሱ ላባቶቻቸው ታሪኩን ሲነግሯቸው የካጋ አባት በጣም ተናደዱ፡፡
እሳቸውም “ወስፈንጥርና ምግብ የሌለው ወጥመድ አይጥ አይዝም፡፡ ይህን ደግመህ ብታደርግ እቀጣሃለሁ፡፡” አሉት፡፡
ይህ እንግዲህ ሰዎች የማይታመኑ ነገሮችን እንዳያምኑ የሚያስጠነቅቅ ሲሆን አታላይ ሰዎችም ንብረታቸውን እንዳይነጥቋቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይመክራል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|