ንጉሱን ማታለል
በአሚኖ ኦጁሎ የተተረከ
አጌንጋ ንጉሱን በማነጋገር ላይ ሳለ “ንጉሱም አንተ ካታለልከኝ ጠመንጃዬን እሰጥሃለሁ፡፡” ብሎ ቃል ገባለት፡፡
ከተወሰነ ጊዜም በኋላ ንጉሱ ለአደን ወደ ጫካ ሲሄድ ይህንን የሰማው አጌንጋ በተቃራኒው አቅጣጫ ሄደ፡፡ ንጉሱ ባያየውም አጌንጋ እየተመለከተ ስለነበር ሰዎችን ወደ ማር የምትመራዋን የማር ወፍ በመምሰል ንጉሱን የማታለል ስራውን ጀመረ፡፡ ከዚያም ንጉሱ ባፏጨ ጊዜ አጌንጋ የወፏን ዝማሬ በማሰማት ንጉሱ ሳያየው ይመራው ጀመር፡፡ ንጉሱ ለረጅም ጊዜ በምስጦች ኩይሳ ዙሪያ ፍለጋውን ካካሄደ በኋላ አጌንጋ ወደተደበቀበት እሾሃማ ቁጥቋጦ ውስጥ ስለገባ ቁጥቋጦው ሰውነቱን ጫጫረው፡፡
አጌንጋም ከተደበቀበት ወጥቶ “የሰማኸው የማሯን ወፍ ሳይሆን እኔን ነው፡፡ አሞኝቼሃለሁና ጠመንጃህን ስጠኝ፡፡” አለው፡፡ ንጉሱም “እሺ አሞኝተኸኛልና ወደ አዛውንቶች ሄደን ፍርዱን እንቀበል፡፡” ብሎ መለሰ፡፡
ወደ አዛውንቶቹም በደረሱ ጊዜ ንጉሱ እንዲህ አለ “አጌንጋ አታሎኛልና ቃል በገባሁለት መሰረት ጠመንጃዬን እሰጠዋለሁ፡፡”
ሰዎቹም “እሱስ ምን አድርጎልሀል?” ብለው ጠየቁት፡፡
ንጉሱም “ምንም አላደረገልኝም፡፡ ነገር ግን ስላሞኘኝ ልገድለው አልፈልግም፡፡ ምክንያቱም ጠመንጃዬን ልሰጠው ቃል ገብቼለታለሁና፡፡” አላቸው፡፡
በዚህም አይነት አጌንጋ በህዝቡ ፊት ጠመንጃውን ተረከበ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|