ቆራጧ ሴት
በአሪዬት ፔታ የተተረከ
ከእለታት አንድ ቀን አንድ ባልና ሚስት እንደተለመደው ሁሉ ባልየው ጠመንጃውን ተሸክሞና አንዳንድ ጊዜ እየተኮሰ ከፊት ከፊት በመሄድ ሚስቱን አስከትሎ ይጓዙ ነበር፡፡ ከጥቅጥቅ ደን አጠገብም እንደደረሱ ሽፍቶችሽፍታ ማለት ወንበዴ ማለት ነው፡፡ ሲመጡባቸው በጣም በመደንገጥ ሮጠው ለማምለጥ ሞከሩ፡፡ ነገር ግን ሚስትየው ባሏን አስቁማው ጠመንጃውን በመንጠቅ ሽፍቶቹ ላይ መተኮስ ጀመረች፡፡ ሽፍቶቹም በጣም ስለፈሩ ጠመንጃቸውን ጥለው ወደጫካው ሸሽተው ገቡ፡፡ እሷም ጥለው የሮጡትን ጠመንጃ ባሏ እንዲያነሳ አድርጋ ጠመንጃዎቹን ተሸክሞ ባሏ ኋላ ኋላ፣ እሷ ፊት ፊት ተከታትለው መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡ ከዚያም የአንድ ባላባት ንብረት ከሆነ ትልቅ ይዞታ አጠገብ ሲደርሱ ሚስትየው አንድ ትልቅ ከበሮ ስላገኘች ጮክ ብላ በመጮህ የድል ዘፈኖችን መዝፈን ጀመረች፡፡
ባካባቢው ያሉ ሰዎችም የባሏን ዘመዶች ጨምሮ ሲሰባሰቡ “በዚህ ሰው እጅግ ማፈር ይገባችኋል! ሚስቱን እንኳን ማዳን ካልቻለ ወንድ አይባልም፡፡” አለቻቸው፡፡
ዘመዶቹም በባልየው ስላፈሩ ገደሉት፡፡ ከዘመዶቹም አንዱ ደፋር ሰው ሚስቱን አግብቶ በደስታ አብረው መኖር ጀመሩ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|