ባሏ የሞተባት ሴት
በኦባንግ ኦቦቲ የተተረከ
በአንድ ወቅት አንዲት ደስተኛ ሴት ነበረች፡፡ ባሏ ከመሞቱ በፊት የፈለገችው ሁሉ ተሟልቶላት ከልጆቿ ጋር ትኖር ነበር፡፡ ልጆቿም ደስተኞች ነበሩ፡፡ በኑሯቸውም ደረጃ ባልና ሚስቱ የተከበሩ ነበሩ፡፡ ባሏ ከሞተ በኋላ ግን ሴትየዋ ኑሮ ከበዳት፡፡
ልጆቿም ደስታ እርቋቸው እናታቸውን እንዲህ በማለት ጠየቋት “ወደፊትስ እንዴት እንሆናለን?”
እሷም “ልጆቼ ሆይ! ኑሮ ያለአባት እንዴት እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡ አባት ያለው ሁሉ ሰብሉ ቡቃያ ሲያወጣ ይደሰታል፡፡” አለቻቸው፡፡
ይህንንም ስትል ልጆቿ ክፉውን ከደጉ በቀላሉ መለየት እንዲችሉ ለማለት ነው፡፡ ሁሉንም ነገር ስታደርጉ ደስተኛና ነፃ ስለምትሆኑ ማንም አይጎዳችሁም፡፡ ክፉ ነገር ግን ማድረግ የለባችሁም፤ ማንም አይረዳችሁምና፡፡
በዚህም ጊዜ ልጆቹ ካላባታቸው እርዳታ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው ተገነዘቡ፡፡
እናታቸውንም ስለተረዷት “የምትነግረን ነገር ሁሉ እውነት ነው፡፡ አሁን አባታችን ስለሞተ አስተማሪያችን እናታችን ናት፡፡” አሉ፡፡
በመጨረሻም “አሁን እቤታችንን ጥለን መሄድ አንችልም፡፡ እዚሁ ቆይተን ችግሮቻችንን በጋራ እንታገላለን፡፡” ብለው ወሰኑ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|