አቾክና አጎቱ
በአኮላ አዋር የተተረከ
አቾክና አጎቱ አሣ ለማጥመድ ወደ ወንዝ ወርደው አቾክ አኮክ የተባሉና በጀርባቸው ላይ ሹል እሾህ ያለባቸውን ብዙ ዓሣዎች ይዞ ወደቤት በመመለስ አበሰላቸው፡፡ አጎቱንም ከእንቅልፉ ቀስቅሶ አብረው እንዲበሉ ጠራው፡፡
እየበሉም ሣለ አጎቱ “ይህንን ዓሣ ከየት አመጣህ?” ብሎ ጠየቀው፡፡
አቾክም የቢራውን አተላ ወደ ወንዙ ይዤ በመሄድ ውሃው ውስጥ ጨመርኩት፡፡ ከዚያም ሌሎች የዓሣ ዝርያዎች ሲመጡ ተውኳቸውና አኮኮች ሲመጡ ራሴን ወደ ወንዙ ወርውሬ በመግባት ነው ይህንን ሁሉ ዓሣ የያዝኩት፡፡ እሾሆቹም ሰውነቴ ውስጥ ሲገቡ ከወንዙ ውስጥ ወጥቼ ከሰውነቴ ላይ ነቃቀልኳቸው፡፡” አለው፡፡
በማግስቱም ጠዋት አጎቱ የቢራውን አተላ ይዞ ዓሣ ሊያጠምድ ወደ ወንዙ ወረደ፡፡ አተላውንም ውሃው ውስጥ ጨምሮ አኮኮቹ ሲመጡ ሲያይ ወደ ወንዙ ውስጥ ተወርውሮ ሲገባ በዓሣዎቹ እሾህ ተወጋጋ፡፡ ከወንዙም ወጥቶ እሾሁን ከሰውነቱ ላይ ሊነቃቅል ቢሞክርም አልቻለም፡፡ ነገር ግን ዶሮዎችን የሚያካክሉና ረጃጅም አንገት ያላቸው አልዋሮ የተባሉ የወፎች ዝርያ የሆነ ህይወቱን ሊያተርፍ መጣ፡፡
አልዋሮውም በመጣ ጊዜ የአቾክ አጎት “እባክህ አሣዎቹን አውጣልኝ::” አለው፡፡
አልዋሮውም እንዲህ አለ “ዓሣዎቹን ከወንዙ ካወጣሁ ትልልቆቹን መብላት እችላለሁ?”
አጎትየውም “አይሆንም” ሲል አልዋሮው ሄዶ በፔሊካን ተተካ፡፡ አባንጎ የተባለውም ፔሊካን ትልልቆቹን ዓሣዎች መብላት እንደሚችል ጠየቀ፡፡ አጎትየው አሁንም አይሆንም አለ፡፡
አለውክ የተሰኘው ማሪቡ ስቶርክ በጣም ትልቅና ሰማያዊ ቀለም ያለው ሲሆን አሳዎችን የሚመገብና አንገቱ ሥር ካለው ከረጢት ውስጥ የሚያኖር ተኪኒ ዶሮን የሚመስል ሆኖ መጠኑ ትልቅ ወፍ ነው፡፡ ይህ ወፍ ግን በተቃራኒው “ትንንሾቹን ዓሣዎች ብቻ ስጠኝ፡፡” ብሎ ጠየቀ፡፡
አጎቱም በዚህ ቢስማማም አልውኩ ግን በማታለል ትልልቆቹን ዓሣዎች በሙሉ በላቸው፡፡
አጎቱ በዚህ ሣይከፋ ትንንሾቹን ዓሣዎች ይዞ ወደቤቱ ሄደ፡፡ እቤት ሲደርስም ጀርባው እየደማ ስለነበር የወንድሙ ልጅ “አጎቴ ምን ሆነሃል?” ብሎ ጠየቀው፡፡
“አንተ እንደነገርከኝ አደረኩ፡፡ አተላውን ወደ ወንዙ ጨምሬ እሾሃማዎቹ አሳዎች ሲመጡ ውሃው ውስጥ ዘልዬ ገባሁ፡፡”
“አይሆንም” አለ አቾክ “እኔ እንደዚህ አድርግ ብዬ አልነገርኩህም፡፡ እኔ እንዳደረኩት አንድ በአንድ እንድታጠምዳቸው ነው የነገርኩህ፡፡” አለው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|