ሰዎችና እንስሳት በሥነ ፍጥረት እንዴት እንደተለዩ
በአክዋይ ጎራ የተተረከ
እንስሳቱና የሰው ልጆች በሙሉ በተሰበሰቡበት እግዚአብሔር “የአጥቢያ ኮከብ ሲወጣና ዶሮ ሲጮህ ቀድሞ የደረሰ የተሻለ ድርሻ ይኖረዋል::” ብሎ ነገራቸው፡፡
መጀመሪያ እግዚአብሔር ጎሽ ነው የሚመጣው ብሎ ሲጠብቅ ለካስ ሰው ነው ራሱን እንደጎሽ በማስመሰል “በውሾች እጅ ያደኩ ነኝ፡፡” ብሎ የተናገረዉ፡፡ ውሾቹም እግዚአብሔር ከጎሽ ጋር ሲነጋገርና “ቀድመህ ና የንጋት ኮከቡንም ባየህ ጊዜ ምርጡን ድርሻ እሰጥሃለሁ፡፡” ሲለው ሰሙት፡፡
ይህንን የሰማው ውሻ ወደ ሰው በመሄድ በጠዋት ተነሳና “ምርጡን ድርሻ ውሰድ፡፡” ብሎ መከረው፡፡
ሰውም የተባለውን አደረገ፡፡ እግዚአብሔርም “አንተ ማነህ?” አለው፡፡
ሰውም “እኔ የውሾች የማደጎ ልጅ ነኝ፡፡ በውሾች እጅ ያደኩ ሰው ነኝ፡፡” አለው፡፡ ከዚያም ጦር ተሰጠው፡፡
ቀጥሎ ጎሽ መጣ
እግዚአብሔርም “ቅድም የመጣው ማነው? መሣሪያዎቹ ሁሉ ተወስደዋል ለአንተና ለሌሎች መከላከያ የሰውነት አካላት ለሌሏቸው እንስሳት የቀረው ቀንድ ብቻ ነው፡፡” አለ፡፡
ስለዚህ ከሰው ተለይተው ቀንድ ተሰጣቸው፡፡ ከዚያም በኋላ ከብቶች ሁሉ የሰው አገልጋይ ሆነው ቀሩ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|