አቾክና ሌሮ ማር በመሰብሰብ ላይ
በቻሜ ክዌር የተተረከ
አንድ ግንዱ የተቦረቦረ ዛፍ ካገኙ በኋላ አቾክ “የአክስቴ ልጅ ሆይ! የጫካ ማር ስትሰበስብ ንቡ እንዲነድፍህ ከዛፉ ጋር መታሰር አለብህ አንድ ሰው ካልታሰረ ማር መሰብሰብ አይቻልም፡፡” አለው፡፡
ይህንንም ካለ በኋላ ዛፉ ላይ አስሮት ጥሎት ሮጠ፡፡ ሌሮም በንቦቹ ክፉኛ ስለተነዳደፈ አከታትሎ ቢጮህም የሚደርስለት ሰው አልነበረም፡፡ በመጨረሻም አንድ እንግዳ ሰው መጥቶ ሲፈታው ሌሮ ከዛፉ ላይ ወደቀ፡፡
ከዚያም ወደ ቤት ሄዶ አቾክን ሲያገኘው በንዴት “ማሩን ሰበሰብክ? አንድ ሰው ከዛፉ ላይ ካልታሰረ ማር መሰብሰብ አይቻልም ያልከውስ እውነት ነው? ለምን እንደዚያ አልክ? ዝም ብለህ ሄደህ ለምን አልሰበሰብክም?” ብሎ ጠየቀው፡፡
አቾክም ሄዶ ማሩን ለመሰብሰብ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|