አቾክና ሌሮ አሣ በማጥመድ ላይ
በቻሜ ክዌር የተተረከ
አቾክ ሌሮን እንዲህ አለው “የአክስቴ ልጅ ሆይ ሌሊቱን ሙሉ አሳ ሳጠምድ አድራለሁ፡፡”
ታዲያ ይህንን ያለው የያዘውን ዓሣ በሙሉ ለራሱ ሊበላ ፈልጎ ነበር፡፡ ሌሮም “ትንኞቹ ያስቸግሩሃል፡፡” አለው፡፡
አቾክም “ምንም ችግር የለም፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡
ከዚህም በኋላ ብቻውን ወደ ዓሣ ማጥመዱ በመሄድ ወጥመዱንና መንጠቆውን አዘጋጅቶ ወንዙ አፋፍ ላይ ቆመ፡፡ ነገር ግን ሌሮ ተከታትሎት ሄዶ በወንዙ አፋፍ ላይ ካለ ሳር ውስጥ ተደብቆ ይከታተለው ጀመር፡፡ አቾክም ዓሣ በያዘ ቁጥር ወደሳሩ ውስጥ እየወረወረ ሲያስቀምጥ ሌሮ ዓሣዎቹን ይለቅማቸዋል፡፡
ዓሣ ማጥመዱን እንደጨረሰ አቾክ የያዛቸውን ዓሣዎች ሰብስቦ በመውሰድ ብቻውን አብስሎ ሊበላ ቢያስብም ዓሣዎቹን ከቦታቸው አላገኛቸውም፡፡
እሱም “እንዴ አንዱን እዚህ ወይም እዚህ ጋ አስቀምጬ አልነበረም?” እያለ ራሱን ይጠይቅ ጀመር፡፡
ከዚያም የቀንድ ዓውጣ ሽፋን በሰውነቱ ላይ ተሰባብሮ ስለነበረ ቆዳው ቆሽሾ ነጭ ሆነ፡፡
ይህንን ያዩ ሁሉ “ምን ሆነህ ነው?” እያሉ ሲጠይቁት ሌሮም ከሰዎቹ ጋር አብሮ “ምን ሆንክ?” ብሎ ይጠይቀው ጀመር፡፡
አቾክም “አንተ ትክክል ነህ፡፡ እንዳልከውም ብዙ ትንኞች ስለነበሩ ነካክሰው ሰውነቴን ሁሉ ነጭ አደረጉት፡፡” አለ፡፡
ሌሮም “አዎ እኔ ትክክል ነበርኩ፡፡ ሌሊቱን ሙሉ እዚያ መቆየት አልነበረብህም::” አለው፡፡
ሆኖም ታዲያ አቾክ ሌሮ ዓሣዎቹን ጠብሷቸው እንደነበረ አላወቀም ነበር፡፡ የምግብ ሰዓት ደርሶ ዓሣዎቹ በቀረቡም ጊዜ አቾክ “ይህ እኔ ይዤው የነበረው ዓሣ አይደለም እንዴ?” ብሎ አሰበ አንድ ጉርሻ እንደጎረሰም “ይህ እነዚያን ነገሮች ይመስላል፡፡” አለ፡፡
ሌሮም ቀበል አድርጎ “የቶቹን ነገሮች የአክስቴ ልጅ? ለምን ዝም ብለህ ችግርህን አታምንም? ስስታም ስለሆንክ ዓሣዎቹን እኔ ወስጄ ጠበስኳቸው፡፡ ይጣፍጣሉ አይደል? አሁን አንተም እየበላህ ነው፤ አይጣፍጥም?” አለው፡፡
አቾክም “አዎ አንተ ትክክል ነህ::” አለው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|