አጌንጋ ንጉሱን አታለላቸው
በኦቦቲ ቻም የተተረከ
አጌንጋ ከንጉሶች ዘንድ ይኖር ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ታዲያ አጌንጋ ሰዎቹ ሁሉ ወደተሰባሰቡበት ስፍራ በመሄድ ጫማውን አውልቆ ንጉሱ በተቀመጡበት መጠለያ የሣር ጣሪያ ላይ አኖረው፡፡ ንጉሱም በመጣ ጊዜ ይህንን ሳያስተውል ቁጭ አለ፡፡ ሰው ሁሉ ቁጭ ብሎ እየተነጋገረ ሳለ አጌንጋ ከንጉሱ አጠገብ በመቀመጥ ጫማዎቹን ለማውረድ ቢሞክርም ስለራቁት አልቻለም፡፡ ለመነሳት ስላፈረም በጉልበቱ በመንበርከክ ጫማዎቹን ለማውረድ ሞከረ፡፡
ንጉሱ ይህንን ባየ ጊዜ እንዲህ ብሎ ጠየቀው “ምን ተቸግረህ ነው አጌንጋ?”
አጌንጋም “ጫማዎቼን ማውረድ ብፈልግም ከእርስዎ አናት ላይ ሆነው ስለራቁኝ ነው፡፡” አለ፡፡
ንጉሱም በመነሳት ጫማዎቹን አውርዶ ለአጌንጋ ሰጠው፡፡ የአጌንጋን ተንኮል ግን አላስተዋለም ነበር፡፡
አጌንጋም እንዲህ አለ “ተመልከቱ ንጉስ አይታዘዝም ብላችሁ ስትነግሩኝ ነበር፡፡ ነገር ግን እኔ ንጉሱን ለማዘዝ ችያለሁ፡፡”
ይህም ሰው በደርግ የስልጣን ዘመን ወቅት በጣም ይቸገር የነበረና በመጨረሻም ወደ ኩባ ተልኮ እዛው አብዶ የቀረ ሰው ነው፡፡ይህ አርፍተ ነገር ስለማን እንደተፃፈ ግልፅ አይደለም፡፡ ደርግ በመንግስቱ ሐይለማርያም መሪነት ኢትዮጵያን ከ 1967-1983 የገዛ ኮሚውኒስታዊ ወታደራዊ አገዛዝ ነው፡፡ ኩባም ይህንን መንግስት ትረዳ ነበር፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|