አጌንጋና በቆሎው
በኦቦቲ ቻም የተተረከ
ከእለታት አንድ ቀን አጌንጋና ኦሜት የተባለው ጓደኛው ጋንቤላ ውስጥ ወደሚገኘው ፒኒኬው ወደተባለ መንደር አብረው ሄዱ፡፡ ከመንደሩም እንደደረሱ በጣም እርቧቸው ስለነበር ፒኒኬው ውስጥ በሚገኝ አንድ የቤተሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተስተናገዱ፡፡ ሰዎቹም በጣም መራባቸውን ባዩ ጊዜ ያልተቀቀለ በቆሎ እሸት ሰጧቸው፡፡
እነርሱም ይህን እሸት በቆሎ እንዴት ልናበስለው እንችላለን ከተባባሉ በኋላ ኦሜት “እስኪ እኔ እንዴት እንደምናበስለው መንገድ ልፈልግ፡፡” አለ፡፡
የማገዶ እንጨት አልነበራቸውም፣ ቁጥቋጦም አልነበረም፣ እንዲሁም ዛፎቹ ሁሉ ከወንዙ ባሻገር ነበሩ፡፡ ባረፉበት አካባቢ ዙሪያውን ለከብቶች መጠበቂያ አጥር የታጠረበት መቃብር ነበር፡፡ ኦሜትም በዚሁ መቃብር ስፍራ በመሄድ ከአጥሩ ላይ እንጨት በመምዘዝ ለበቆሎ ማብሰያ አመጣ፡፡
ሰዎቹም እንጨቱን እየሰበረ ባዩት ጊዜ እንዲህ እያሉ ጮሁበት “ልጃችንን የገደለውን ቡዳ አገኘነው፤ አሁን ደግሞ ነፍሱን ሊገድል በድጋሚ የመጣው በቀብሩ ስነ ስርአት ወቅት መሬቱን የመደልደሉ ስራ እስካሁን ስላልተጠናቀቀ ነው፡፡”
በዚህን ጊዜ አጌንጋ የጓደኛውን ሕይወት ለማዳን በማሰብ ኦሜትን ሄዶ ከያዘው በኋላ በመደባደብ ተያይዘው ወደቁ፡፡
ሰዎቹም በመጡ ጊዜ አጌንጋ እንዲህ አለ “ተመልከቱ እዚህ ይዤ የመጣሁት የአእምሮ በሽተኛ ሰው ነውና አትጉዱት፡፡”
ሰዎቹም ይህንኑ ሰምተው በመጨረሻ ዝም ካሉ በኋላ ሁለቱ ጓደኛማቾች እንዴት እንደተራቡ አይተው በቆሎዋቸውን ያበስሉ ዘንድ አጥሩ ላይ ያለውን እንጨት እንዲጠቀሙ ፈቀዱላቸው፡፡
ወደሚቀጥለው > |
---|