ጋንያ ስስታሙ ሰው
በኒያል ጋትች የተተረከ
ቱት በመባል የሚጠራው ጋንያ ቱት የተባለ ሰው ከቤቱ ውስጥ ብዙ ሃብት የነበረውና ሃብታም ስስታም ሰው ነበር፡፡ አንድ ቀን ሚስቱ ያበሰለችለትን ትልቅ ስጋ መጋዘኑ ውስጥ ቁጭ ብሎ ይበላ ጀመር፡፡
ውሻውም መጥቶ ሰውየውን ሲበላ ቢያየውም ጋንያ ፊቱን ከውሻው አዙሮ መብላት ሲጀምር ውሻው ወደ መጋዘኑ በር ዘሎ ተመለሰ፡፡
ጋንያም ወደ ኋላው ሲዘል ከተቀመጠበት ቦታ አጠገብ ያላስተዋለው ጉድጓድ ስለነበር ከመቀመጫው ተፈንግሎ ምግቡን በሙሉ ደፍቶት ጉድጓዱ ውስጥ ወደቀ፡፡
አንድ ልጁም ከወንድሙ ልጅና ከሰውየው ሴት ልጅ ህፃን ጋር በስፍራው ስለነበሩ ህፃኗ ልጅ ማልቀስ ጀመረች፡፡
“ምን ሆነሽ ነው?” ብለው ጠየቋት፡፡
እሷም “የማለቅሰው የአያቴ ምግብ በሙሉ ተደፍቶ ስለተበላሸ ነው፡፡” አለች፡፡
ጋንያም በጣም ተናደደ፡፡
“ለምግቡ አታልቅሺ::” አላት፡፡ “አንቺ ደደብ ልጅ፤ እኔስ? ለእኔ ለምን አላለቀስሽም?” አላት፡፡
ከዚያም የተሰበረ እግሩን እያስታመመ ለሶስት ቀናት በቤት ውስጥ ቆየ፡፡ ከሶስት ቀናት በኋላም ቀስ ብሎ በጥንቃቄ እየተራመደ ከሶስት ጓደኞቹ ጋር ተቀመጠ፡፡ በጣም እየተጫወቱና እየተሳሳቁ ከቆዩ በኋላ ጓደኛው ሳያውቅ እግሩን መታው፡፡
በዚህን ጊዜ ጋንያ “እህህ እግሬን ሰበርከው እናም መክፈል ስላለብህ አስር በሬዎች ስጠኝ::” አለው፡፡
ወደ ዳኛም ሄዱ፡፡
ጋንያም የተሰበረ እግሩን ለዳኛው እያሳየ “ይህ ሰው እግሬን ሰብሮታል፡፡” አለ፡፡
ዳኛውም ለእርሱ ስለፈረደለት የጋንያ ጓደኛ አስር ላሞች ሰጠው፡፡
ጋንያ ከበሬዎቹ አንዱን ባረደ ጊዜ ሌላ ጓደኛው መጥቶ “እባክህ የበሬውን አንድ እግር ስጠኝ፡፡” ብሎ ጠየቀው፡፡
“እሺ” አለ ጋንያ “ታዲያ በምትኩ ምን ትሰጠኛለህ?”
ሰውየውም “እኔ ደግሞ በሬዬን ሳርድ አንድ እግሩን እሰጥሃለሁ፡፡” አለው፡፡
በዚህም ተስማምተው ሰውየው የበሬውን አንድ እግር ወሰደ፡፡
ከአምስት ቀናት በኋላም ጋንያ ወደ ጓደኛው ቤት በመሄድ “ቃል የገባኸውን የበሬ እግር እባክህ ስጠኝ?” ብሎ ጠየቀው፡፡
ሰውየውም “እሺ፣ ግን እባክህ በሬ እስከማርድ ድረስ ጊዜ ስጠኝ፡፡” አለው፡፡
ጋንያ ግን ሄዶ የጓደኛውን አንድ በሬ ካረደ በኋላ አንድ እግሩን ይዞ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ ጓደኛውም በጣም በመበሳጨት ከበሬዎቹ አንዱን ያለ እርሱ ፈቃድ በማረዱ ከሰሰው፡፡
ጋንያም “በሬውን አልወሰድኩም፡፡ እኔ ለሰጠሁህ አንድ እግር ብቻ ምትኩን ነው የወሰድኩት፡፡” አለው፡፡
ዳኛውም ወደ ጓደኛው ዞሮ “ጋንያን ምን እንዳደርገው ነው የምትፈልገው?” አለው፡፡
እሱም “አንዱን በሬ እረድበትና አንድ እግሩን እወስዳለሁ፡፡” አለ፡፡
ከዚያም ጋንያ አንዱን በሬ አርዶ አንድ እግሩን ለጓደኛው ሰጠ፡፡
ከዚያምየዚህ ታሪክ አጨራረስ ግልፅ አይደለም፡፡ “እንግዲህ በሬዬን አርጄ አንድ እግሩን ስለሰጠሁህ አንተም ባለፈው የወሰድከውን እግር መልስልኝ?” አለው፡፡
እናም ሰውየው ሄዶ አንድ በሬ ካረደ በኋላ ለጋንያ ሰጠው፡፡ ታሪኩም ይኸው ነው፡፡
This is the story.
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|