ወጣቱ እንግዳ
በኦፒው አምዎንግ የተተረከ
በአንድ ወቅት ብቻውን የሚኖር አንድ አዛውንት ሰው ነበር፡፡ ብቻውን ይበላል፡፡ ብቻውን ይተኛል፡፡
ታዲያ ከእለታት አንድ ቀን አንድ ወጣት ሰው ራት ከመበላቱ በፊት አዛውንቱ ቤት ይደርሳል፡፡ አዛውንቱም ሰው በዚህ ደስተኛ አልነበረም፡፡ ምግቡም ለሁለቱ የሚበቃቸው ስላልመሰለው እራቱን ከእንግዳው ጋር መካፈል አልፈለገም ነበር፡፡ ነገር ግን በመጨረሻ አብረው እንዲበሉ ከወሰነ በኋላ እሱ ቀስ እያለ ይመገብ ጀመር፡፡ ሆኖም ምግቡ ብዙ ነበር፡፡ ወጣቱም ሰው በትክክለኛ አበላል ተመግቦ ስለጠገበ ቀድሞ መብላት አቆመ፡፡
አዛውንቱም ሰው እፎይታ ተሰምቶት ለራሱ እንዲህ አለ “ወጣቱ ሰው ከእኔ ቀድሞ ጠገበ፡፡”
ከዚያም ምግቡን ወደራሱ በመሳብ ቢበላም ሊጨርሰው አልቻለም፡፡
የዚህ ተረት መልዕክትም ነገሮች ከመሆናቸው በፊት ወይም ከሆኑ በኋላ አትጨነቅ የሚል ነው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|