የውሻ ድምፅ መጥፋት
በቲቶ ባንጌ የተተረከ
ከብዙ ዘመናት በፊት ገና ዓለም ስትፈጠር ሰውና ውሻ ጓደኛሞች ነበሩ፡፡ ውሾችም የንግግር ስጦታ ስለነበራቸው ከሰው ጋር ይነጋገሩ ነበር፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ሰዎችና ውሾች ጭቅጭቅ ውስጥ ስለገቡ ይህንኑ ንስሃ ይገቡ ዘንድ ወደ አንድ የተቀደሰ አስማተኛ ዶክተርና ቄሶች ወዳሉበት ቦታ ሄዱ፡፡
ሊሄዱ የሚችሉበት ምርጡ ቦታ ሰማይ ብቻ መሆኑን ተስማምተው ወደዚያው በመሄድ ችግራቸውን በዝርዝር ካቀረቡ በኋላ ሰማይ ቤት እሳት መኖሩን አዩ፡፡ ጥሩና የሚሞቅ መሆኑንም ተገነዘቡ፡፡
ችግራቸውንም ከፈቱ በኋላ በመመለስ ላይ እያሉ ውሻው ሰውየውን “አንተ ከፊት ፊት ሩጥ እኔም እደርስብሃለሁ፡፡” አለው፡፡ እናም ከዚያ ቦታ በሩጫ ሲወጡ ውሻው እሳቱን በጭራው ይዞ ተከታትለው መጡ፡፡ በዚህም ዓይነት እሳት ወደ ምድር ወረደ፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ሰዎችና ውሾች አብረው ወደ አደን ሄዱ፡፡
ከሩቅም አንበሳ ባዩ ጊዜ ሰዎቹ ውሾቹን “አንበሳ ጠላታችን ነው፡፡ ያደነውን እንስሳ ሁሉ ይበላብናል፡፡” አሏቸው፡፡
ወደ ጫካው ውስጥም በገቡ ጊዜ አንድ ጎሽ አግኝተው ገደሉት፡፡ ጎሹንም ከገደሉት በኋላ እጅና እግሮቹን ቆርጠው ከታተፉት፡፡
ከመመገባቸው በፊት ግን መጀመሪያ ማድረግ ያለባቸው ትንሽ የሥጋ ቁራጮች ሩቅ ቦታ ላሉት መንፈሶች መስጠት ነበር፡፡ ስለዚህ ጎሽ በጣም ትልቅ እንስሳ ስለሆነና ለሸክም ስለማያመች አንድ ቆንጆ ጮማ ስጋ የውሻው አፍ ውስጥ አኑረው ሲያበቁ ውሻው ስጦታቸውን ለመንፈሶቹ እንዲያደርስ ነገሩት፡፡
ውሻውም ሮጦ ሮጦ ስለደከመውና እያለከለከ ስለነበረ ምላሱን ግን ማውጣት አልቻለም፡፡ ስለዚህ አፉ ውስጥ የያዘውን ሥጋ መሬት ላይ አሳርፎ ትንሽ አረፍ አለ፡፡ ውሻውም እረፍት እያደረገ ሳለ ምራቁን ውጦ ስለነበር የስጋውን ጣዕም ቀምሶ ሥጋው ጥሩ መሆኑን አወቀ፡፡ ከዚያም ሥጋውን አንስቶ ሩጫውን ቀጠለ፡፡ ሆኖም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ውሻው ሥጋውን የመብላት ፍላጎቱ ስለጠናበት ሥጋውን ከበላ በኋላ ወደ ሰዎቹ እየሮጠ ተመለሰ፡፡
ሰዎቹም ውሻውን አዩትና “ውሻ ሆይ ሥጋውን ለመንፈሶቹ አደረስክ?” ብለው ጠየቁት፡፡
ውሻውም ጭራውን ቆልፎ ጆሮዎቹን ወደኋላ በማስተኛት አላዘነ፡፡
ሰዎቹም “ውሻው ምን ሆነ?” ብለው ካሰቡ በኋላ ውሻው ከሰማይ ያመጣውን እሳት በመጠቀም ስጋውን ጠብሰው የተወሰነውን በሉ፡፡
ከዚያም “ምናልባት ውሻው መብላት አልፈለገ ይሆናል፡፡” አሉ፡፡ በኋላም እንደገና ወደ ውሻው ተመልሰው ቢያነጋግሩት እንዲያደርስ የተሰጠውን ሥጋ ለመንፈሶቹ ባለማድረሱ ድምፁ ስለተወሰደበት መልስ ሊሰጣቸው አልቻለም፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|