ጨካኙ አባት
በአቻን ኦኮኝ የተተረከ
አንዲት ሴት ልጅ የነበረው አንድ ሰው ነበር፡፡ እሱም “እባክሽ አታግቢ፡፡ ህይወትሽን በሙሉ አብረሺኝ እየኖርሽ ተንከባከቢኝ፡፡” አላት፡፡
ከዚያ ግን ከሩቅ የመጣ ሰው አፍቅራ በድብቅ ፍቅሯን መለዋወጥ ጀመረች፡፡ የመንደሩ ሰው ሁሉ የአካባቢውን ሰው ማግባት እንደማትችል ስለሚያውቅ ነው የሩቅ ሰው የፈለገችው፡፡ በመጨረሻም ፀነሰች፡፡
አባቷም ይህንን በተመለከተ ጊዜ “ምን ነካሽ? ማንንም እንዳታገቢ ብዬ አልነገርኩሽም ነበር? አንቺ ግን አረገዝሽ፡፡ ለምንድነው እንደዚህ ያደረግሽው?” አላት፡፡
እሷም “እኔ የተወለድኩት እንዴት ነበር? ካለምንም ልጆች ዘሬን ሳልተካ ኖሬ እንድሞት ነው የምትፈልገው? እኔ አግብቼ ልጆች እንዲኖሩኝ እፈልጋለሁ፡፡ አሁን እንግዲህ ነፍሰ ጡር ነኝ፡፡ ባልም አለኝ፡፡ የፈለከውን ልታደርግ ትችላለህ፡፡” አለችው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|