አፄ ቴውድሮስና ሌባው
በወርቁ መርሻ የተተረከ
በአጼ ቴውድሮስንጉስ ቴውድሮስ 2ተኛ ከ1847-1860 ድረስ የኢትዮጵያ ንጉስ ነበሩ፡፡ ዘመነ መንግስት ላሞችንና የቤት እንስሳትን የሚሰርቁ ብዙ ሌቦች ነበሩ፡፡
ነዋሪዎቹም ወደ ጃንሆይ ሄደው “ሌቦች በቁጥር እየጨመሩና በጣም እያሰቃዩን ነው፡፡” ብለው አቤት አሉ፡፡
ስለዚህ ንጉስ ቴውድሮስም የሚከተለውን አዋጅ አስነገሩ “በዚህ ምንም ሃሳብ አይግባችሁ፡፡ ሌባ ሲሰርቅ ባያችሁ ጊዜም በንጉስ ቴውድሮስ ይዘንሃል! ቁም! በሉት፡፡”
ታዲያ አንድ ቀን አንድ ሌባ ከአንድ ሰው ቤት ገብቶ ላሞችና በጎችን ሊሰርቅ ሲል ባለቤቱ ከእንቅልፉ ነቅቶ ይደርስበታል፡፡
ባለቤትየውም “በንጉስ ቴውድሮስ ይዤሃለው! ቁም!” ሲለው ሌባለውም አዋጁን በማክበር ቆሞ ጠበቀ፡፡ ነገር ግን ባለቤቱ ጦር ወርውሮበት ስለነበር ጦሩም ከወገቡ ላይ ተሰክቶ ሌባውን ክፉኛ ቢያቆስለውም ህክምና ተደርጎለት ሙሉ ለሙሉ ዳነ፡፡
በኋላ ሌባው ወደ ጃንሆይ ሄዶ “አዩ ጃንሆይ! አራዊትና ሰዎች ሁሉ በእርሶ አዋጅ ስለሚገዙ አንድ ሰው ‘ቁም! በንጉስ ቴውድሮስ ይዤሃለው’ ሲለኝ እኔም አዋጁን አክብሬ ብቆምም ሰውየው ጦር ወርውሮ አቆሰለኝ፡፡ ማምለጥ እችል ነበር፡፡” ብሎ ክስ አቀረበ፡፡
ንጉሱም የጦር ወርዋሪውን ቤተሰብ በሙሉ ጠርተው ሰውየው ካገር እንዲባረርና ለማኝ ሆኖ እንዲኖር ከፈረዱ በኋላ ንብረቱንም ሁሉ ለሚስቱ፣ ለልጆቹና ለሌባው አከፋፈሉ ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|