ራስ ሐይሉ በጄኔቫ
በወርቁ መርሻ የተተረከ
የጎጃም አገረ ገዢ የነበሩ ራስራስ ከንጉሱ ወይም ከአፄው ቀጥሎ የሚገኝ ከፍተኛው የኢትዮጵያ ማዕረግ ነው፡፡ ሐይሉራስ ሐይሉ ከ1860-1951 በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የጎጃም ግዛት አስተዳዳሪ ነበሩ፡፡ የተባሉ አንድ ሰው ነበሩ፡፡ ኢትዮጲያን የተባበሩት መንግስታት አባል ለማድረግ ከአፄ ሃይለስላሴ ጋር ወደ ጄኔቫ ይጓዛሉ፡፡ በኋላም ወደ ኢትዮጲያ በመመለስ ላይ እያሉ ሮምን ሲጎበኙ አንድ ሱቅ ውስጥ ገብተው “ይህ መላጫ ስንት ነው?” ብለው ይጠይቃሉ፡፡
“እንደዚህ ያለውን መላጫ በውድ ዋጋ ነው የምንሸጠው፡፡ ለመሆኑ እንደዚህ አይነቱን ውድ መላጫ በድሃ አገራችሁ ላይ ምን ያደርግላችኋል?” ብሎ ሻጩ በማሾፍ ጠየቀ፡፡
ራስ ሐይሉም “ይህ አንተን አያገባህም፡፡ ዋጋውን ብቻ ንገረኝና ሽጥልኝ፡፡ ምን እንደማደርግበት እኔ አውቃለሁ፡፡ የህዝቤም ፀጉር በጣም ለስላሳ ነው፡፡” አሉት፡፡
በዚህም ሁኔታ መላጫውን ገዝተው በመመለስ አዲስ አበባ ውስጥ ፀጉር ማስተካከያ ቤት ከፈቱ፡፡ ሮም በነበሩም ጊዜ አንድ ሰው “እናንተ ጥቁር ሰዎች ዝንጀሮ ነው የምትመስሉት፡፡” ሲላቸው ራስ ሐይሉም “አዎ! ሁለታችንም ዝንጀሮ ነው የምንመስለው እኔ ፊቷን ስመስል አንተ መቀመጫዋን ትመስላለህ::” ብለውት ነበር ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|