አይጥና እንቁራሪት
በስንታየሁ መለሰ የተተረከ
በአንድ ወቅት አባ አይጦና እማይ ጉርዲት የተባሉ ሁለት ሰዎች ነበሩ፡፡ ሲሄዱ፣ ሲሄዱ በመንገዳቸው ላይ ትንሽ ስንዴ ያገኛሉ፡፡
አባ አይጦም “እንብላው::” አለ፡፡
ጓደኛውም “አይ! አንብላው፡፡” አለች፡፡
በመጨረሻም በመብላቱ ተስማምተው ይፈጩት ጀመር፡፡ እንቁራሪቷም ስንዴውን ፈጭታ ስትጨርስ በውሃ ደባልቃ ሊጥ ማቡካት ትፈልግና በቂ ውሃ ታጣለች፡፡ ታዲያ በሽንቷ ልታርሰው ፈልጋ መሽናት ስትጀምር ፈሷን ስለፈሣች ዱቄቱ በኖ ጠፋ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|