አለቃ ገብረሃና
በስንታየሁ መለሰ የተተረከ
በአንድ ወቅት አንድ አለቃ ገብረሃና የተባሉ ሰው ነበሩ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ከቤተክርስቲያን በመመለስ ላይ ሳሉ አንዲት ሴት እንስራ ተሸክማ ያገኟታል፡፡
“እንደምን ዋልሽ?” አሏት፡፡
“ደህና እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ እርሶ ደህና ነዎት?” አለቻቸው፡፡
በመቀጠልም “አባቴ ሆይ! አንድ የማዋይዎት ትልቅ ችግር አለኝ፡፡” አለቻቸው፡፡
“ውይ ልጄ! ምነው?”
“ጎረቤቶቼ ሁልጊዜ እናንተ ሸክላ ሰሪዎችና ሸማኔዎችበአማራ የድሮ ባህል ሸክላ ሠሪዎችና ሸማኔዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ዝቅ ያለ ቦታ ነበራቸው፡፡ እያሉ ይሰድቡኛል፡፡”
“ልጄ ጎረቤቶችሽ ሳይሆኑ የምትሰሪው እንስራ ነው የሚሰድብሽ፡፡” አሏት ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|