የጅብ (የአህዮቹ) ከንፈሮች
በመጋቢ እንየው ገሠሠ ተተረከ
በአንድ ወቅት ጅብ ልጅ ሞቶበት አህዮች በሙሉ ለቅሶ ሊደርሱት ይሄዳሉ፡፡
አህዮቹ ለምን መሄድ ፈለጉ?
“እንግዲህ ጅቦች ሁሌም ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ እናም ለቅሶ ብንደርሰው ምናልባት በመደሰት ጓደኞቹ ሊያደርገን ይችላል፡፡” ብለው አሰቡ፡፡
ሆኖም አንድ ጅብ በሩቅ እንዲህ እያለ ያለቅስ ነበር፤
“ሁሌም ድምፅህ የሚሰማ
ምንም ሩቅ ብትሆን
ድምፅህ የትም ይሰማል፡፡
እንዴትም ብትፀዳዳ
ኩስህ ሁልጊዜም ነጭ ነው::
ልጅህ ምን ገጠመው?
አንተን ከመሰለ ታላቅ ፍጡር
እንዴት ልጅ ይሞታል?”
ሁሉም እርሱን ተከትለው ማልቀስና ማንባት ጀመሩ፡፡
አንድ ሌላ ጅብም እንዲህ ሲል በግጥም መለሰ፤
“ይህንን ማለትህ እጅግ ደስ ያሰኛል
ለልጃችን የገጠምከው ግጥም እጅግ ደስ ያሰኛል
ታዲያ ምንም እንኳ ግጥምህ ቢያምር
ሃዘንተኞቹ የሚበሉት የለም፡፡”
አንድ አህያም እንዲህ አለ፤
“እግዜር ያፅናህ፡፡ እኛም እንግዲህ እንሂድ” ብለው ተነሱ፡፡ በመሄድ ላይ እያሉም ደጃፉ ላይ ያለ አንድ ጅብ “ሃዘንተኞቹ የሚበሉት ስለሌለ የላይኛውን ከንፈራችሁን ስጧቸው፡፡” አለ፡፡
በዚህም ዓይነት ከንፈሮቻቸው ተቆረጡ፡፡ ይኸው ጅብ ወደ ሌሎች ጓደኞቹ ሄዶ “በልጅህ መሞት እየሣቁ ዝም ብለህ ትለቃቸዋለህ?” አለ፡፡
ይንንም በማመካኘት አህዮቹን በሙሉ በሏቸው፡፡
የዚህ ተረት ተራኪ ተረቱን እንዲህ ሲል አበቃ፤
“ተረቴን መልሱ”
አድማጮቹም እንዲህ ሲሉ መለሱ
“አፌን በጨው አብሱ፡፡”
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|