ሰነፉ ተማሪ
በካሣ አላምረው የተተረከ
አንድ ቀላል ሂሣብ እንኳን የማይገባው ሰነፍ ተማሪ ነበር፡፡ አንድ ቀን ታዲያ መምህሩ ስለመቀነስ እያስተማሩ ሳለ ተማሪው ስላልገባው መምህሩ ምሳሌ ይሰጡት ጀመር፡፡
እንዲህም አሉት “አምስት በጎች በረት ውስጥ ቢኖርህና አንዱ ሾልኮ ቢያመልጥ ስንት ይቀርሃል?”
ተማሪውም “ጌታው እረ ምንም አይቀረኝ” አላቸው፡፡
መምህሩም በመበሳጨት “ይህ እንዴት አይገባህም?” ብለው ጮሁበት፡፡ ተማሪውም እያለቀሰ
“እረ ጌታው የበጎችን አመል ጠንቅቄ ነው የማውቀው አንዲቷ ካመለጠች ሌሎቹም ተከትለዋት ነው የሚጠፉት፡፡” አላቸው፡፡
በዚህም ጊዜ መምህሩ ሲስቁ ክፍሉ በሙሉ ሳቀ፡፡
< ወደኋላ |
---|