ዛፎቹ
በችሎት አማረ የተተረከ
ከዕለታት አንድ ቀን በዓለም ዙሪያ ያሉ ዛፎች ተሰባስበው ስለ ችግሮቻቸው ይወያዩ ነበር፡፡
ከመሃከላቸውም አንዱ እንዲህ አለ “የእኛ ትልቁ ችግር የደን መመንጠር ነው፡፡ ይህም ድርጊት የሚፈፅምብን መጥረቢያበኢትዮጵያ የመጥረቢያ ዛቢያ የሚሰራው ከተጣመመ እንጨት ነው፡፡ የመጥረቢያው አናት በተቆለመመው በኩል ይሰካል፡፡ በተባለ መሣሪያ ነው፡፡ ስለዚህ ጠላታችን የሆነውን መጥረቢያን ማጥፋት አለብን፡፡”
ብዙዎቹም በዚህ ሃሳብ ዙሪያ አስተያየት በመስጠት መጥረቢያ ነው የሁልጊዜ የስቃያችን ምንጭ ይቆርጠንና ቢያሻው ለማገዶ አሊያም ለቤት ዕቃ መሥሪያ፤ እረ ምኑ ቅጡ! ስለዚህ አንድ መላ ፈልገን ይህንን ጠላታችንን ማጥፋት አለብን፡፡ ብለው መከሩ፡፡
አንድ ባህር ዛፍምከ1881-1985 ድረስ ኢትዮጵያን የገዙት አፄ ምኒሊክ ወደ 19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ባህርዛፍን ከአውስትራሊያ ወደ ኢትዮጵያ አስገቡ፡፡ ፈጥኖ ማደጉ፣ ለማገዶነትና ለግንባታ አመቺ መሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት እንዲዳረስ አድርጎታል፡፡ እጁን አውጥቶ “ጠላታችን ግን መጥረቢያ አይመስለኝም፡፡” አለ፡፡
በዚህን ጊዜ ሁሉም ዛፎች ወደርሱ ዞረው እንዴ! ምን ማለትህ ነው? እሱ ካልሆነ ታዲያ ማን ሊሆን ይችላል?” ብለው ጮኹበት፡፡
ባህር ዛፉም ንግግሩን እንዲህ ሲል ቀጠለ “አያችሁ እኔ ከልቤ ነው የምላችሁ ጠላታችን መጥረቢያ አይደለም እኛው ራሳችን ነን፡፡ ሁላችንም መጣመም ትተን ቀጥ ብለን ብናድግ ኖሮ መጥረቢያ አጀታ አይኖረውም፤ እኛም ከመቆረጥ2 እንድን ነበር፡፡
ስለዚህ ከዚህ በኋላ ሁላችንም ሳንጣመም ቀጥ ብለን በማደግ መጥረቢያውን እጀታ መሳሳት አለብን፡፡”
በዚህም ጊዜ ሁሉም ዛፎች አጨበጨቡለት
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|