ገመሬ ዝንጀሮና ተማሪው
በችሎት አማረ የተተረከ
በአንድ ወቅት ተማሪው የሚያደርገውን እያየ እርሱም ድርጊቱን የሚደግም ዝንጀሮ ነበር፡፡ የተማሪው መማሪያ ደብተር ውስጥም እየፃፈ ያስቸግረው ነበር፡፡
ታዲያ በዚህ ድርጊት የተበሳጨው ተማሪ አንድ ቀን የሰላ ቢላዋ ይዞ መጥቶ በደነዙ በኩል አንገቱን የሚያርድ መሰለ፡፡ ዝንጀሮውም ይህንን ያያል፡፡ ተማሪውም ዝንጀሮው እንደተመለከተው ባየ ጊዜ ቢላዋውን አዚያው ትቶ ሄደ፡፡
ዝንጀሮውም እንደልማዱ መጥቶ ቢላዋውን በማንሳት ራሱን አረደ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|