የእንስሳቱ ንጉሥ
በችሎት አማረ የተተረከ
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ አንበሳ ከሁሉም የዱርና የቤት እንስሳት ዘንድ እየዞረ “እናንተ! የእንስሳት ሁሉ ንጉስ ማነው?” ብሎ ሲጠይቃቸው እነርሱም “አንተ ነሃ!” ይሉት ነበር፡፡
ቀበሮን አግኝቶ ይህንኑ ቢጠይቃት እንደዚያው መለሰችለት፡፡ ሁሉንም እንስሳት በዚህ ሁኔታ ካዳረሰ በኋላ በመጨረሻም ወደ ዝሆን ሄዶ ጥያቄውን ቢጠይቀው ዝሆኑ መልስ ሳይሰጥ “ወደ እኔ ዘንድ ቅረብ” ብቻ አለው፡፡ አንበሳውም ወደ ዝሆኑ በተጠጋ ጊዜ ዝሆኑ አንበሳውን አንዴ ብድግ አድርጎ ወደ ሰማይ ቢወረውረው አንበሳው ከመሬት ተላትሞ ከፉኛ ተጎዳ፡፡
አንበሳውም ቀና ብሎ ዝሆኑን እያየ “ንጉስ እኔ ነኝ ማለት ስትችል ይህንን ማድረግ ለምን አስፈለገ::” አለው፡፡ ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|