ሞኞቹ ወላጆች
በካሣ አላምረው የተተረከ
በአንድ ወቅት ብዙ ልጆች የነበራቸውና ከልጆቻቸው መብዛት የተነሣ የማይወዷቸው ሞኝ ቤተሰቦች ነበሩ፡፡ ከልጆቹም አብዛኞቹ ገና በጨቅላነታቸው ግራ እጃቸው ከላሞቹ ጭራ ጋር እየታሰረ ወደ ዱር ስለሚሰደዱ ሞተው አለቁ፡፡ እጃቸው ካላሞቹ ጭራ ላይ እየተነቀለ ስለሚቀር ደም ፈሷቸው ይሞቱ ነበር፡፡
ታዲያ አንዷ ላም ጭራዋ ላይ ተቆርጦ የቀረውን እጅ ይዛ ወደቤት ስትመለስ ያዩት ወላጆች ልጁን ፍለጋ ሲሄዱ አስከሬኑ መንገድ ላይ ወድቆ ያገኙታል፡፡ አፉም በጉንዳኖች ተሞልቶ ነበር፡፡
እነርሱም “አሃ! ጉንዳኖች እየበላ ነበር!” አሉ፡፡ “የሞተውም በጣም ብዙ ጉንዳን በልቶ ነው፡፡”
አባትየውም “በል ተነስ!” እያለ በዱላ ቢደበድበውም ልጁ ሞቷል፡፡ ከዚያም ተመልሰው ለጎረቤቶቻቸው ስለሁኔታው ሲነግሯቸው ጎረቤቶቹም “ወይ ጉድ! ወይ ጉድ! አንድ ፍሬ ልጅ ላም ጭራ ላይ ታስሮ! እንዴት እንደዚህ ታደርጋላችሁ? ካለፈውስ ስህተታችሁ አትማሩም እንዴ? ልጆቻችሁን እንደዚህ አድርጋችሁ ከምትገድሏቸው እናንተው ራሳችሁ ብትሞቱ ይሻላል፡፡” አሏቸው ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|