የተሰረቀው ሥጋ
በካሣ አላምረው የተተረከ
በአንድ ወቅት በወሎወሎ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰሜን ምስራቅ አገር ግዛት ነው፡፡ ክፉ ረሃብ ገብቶ አንድን ቤተሰብ በፅኑ ይጎዳዋል፡፡ የነበራቸውንም ነገር ሁሉ በልተው የቀራቸው አንድ በሬ ብቻ ነበር፡፡ ችግሩም ሲጠናባቸው በሬውን አርደው ለመብላት ተስማምተው ካረዱት በኋላ ሥጋውን በቤታቸው ግድግዳዎች መሃከል ገመድ ላይ ከሰቀሉት በኋላ ለማገዶ የሚሆን እንጨት ለቀማ ይሄዳሉ፡፡ በመንገዳቸውም ያጋጠማቸው አንድ ሰው የጎረቤታቸውን ቤት ይጠይቃቸዋል፡፡ እነእርሱም የራሳቸው ቤት በማመላከት ከእነርሱ ቤት አጠገብ እንደሆነ ነግረውት የእነርሱ ቤት ግን እንዳይገባ አስጠንቅቀው ይሰዱታል፡፡ ሰውየው ግን የሰጡትን እቅጣጫ በመከተል ወደ እነርሱ ቤት ገብቶ ሥጋውን ይበላ ጀመር፡፡
ማገዶውንም ለቅመው ሲመለሱ ስጋው በመሉ ተበልቶ የቀረው አጥንት ደግሞ በዝንብ ተወሮ ያገኙታል፡፡
ባልየውም “ዝንቦቹ ናቸው ሥጋውን የበሉት፡፡” ሲል ሚስቱም በዚሁ ተስማማች፡፡
ዝንቦቹንም ለመበቀል ሲል ለመግደያ የሚሆን ትልቅ ዱላ አዘጋጀ፡፡ ታዲያ ዝንቦቹን ሊገድል በሚሰነዝረው ዱላ የቤት ዕቃውንና ቁሳቁሶቹን ሰብሮ ጨረሰ፡፡ በመጨረሻም አንዲት ዝንብ ከሚስቱ አፍንጫ ላይ ስታርፍ ሚስትየው ቃል ሳትተነፍስ ቀስ ብላ አሳየችው፡፡ በዚህም ጊዜ ባልየው ዱላውን እንስቶ አፍንጫዋን ቢላት ወዲያው ሞተች፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|