ሞኙ ገበሬ
በካሣ አላምረው የተተረከ
በአንድ ወቅት ምሳውን እየያዘ ወደ እርሻ ቦታው ይሄድ የነበረ ገበሬ ነበር፡፡ ምሳውንም ሁልጊዜ በስድስት ሰዓት ይበላ ነበር፡፡ ታዲያ ምሳውን በሚበላ ጊዜ በሬዎቹን በፍፁም አይፈታም ነበር፡፡ ምሳውንም ለሁለት ከፍሎ ግማሹን አንድ ቦታ ግማሹን ደግሞ ሌላ ቦታ ያስቀምጥ ነበር፡፡ አንድ ጉርሻ ከአንድ መዳረሻ ይጎርስና ሌላውን ከሌላው መዳረሻ እየጎረሰ ያለእረፍት እየበላ ያርስ ነበር፡፡
እንደዚህም እያደረገ ሳለ አንድ አሞራ መጥቶ አንዱን የምሳ እቃ ወስዶ እየጮኸ ምሳውን ይበላበት ጀመር፡፡
ገበሬውም አሞራውን እየረገመ እንዲህ አለው፡፡ “የጎዳኸኝ መስሎህ ይሆናል፡፡ በእርግጥ ጓደኞችህ በበረሃ ሲሰቃዩ አንተ ይህንን የመሰለ ጣፋጭ ምግብ ማግኘትህ ትልቅ ዕድል ነው፡፡”
በዚህም ምክንያት ገበሬው “ጎዳኸኝ” እየተባለ ይጠራ ጀመር፡፡
ታዲያ ይኸው ገበሬ ከዕለታት አንድ ቀን በክረምት ብዙ ሲያርስ ውሎ ወደቤቱ ይመለሳል፡፡ ሚስቱም በጣም ጥሩ እራት አብስላና የሚሞቀው እሳት አያይዣ ትጠብቀው ነበር፡፡
እሱም እሳቱ አጠገብ ቁጭ ብሎ እራቱን መብላት ጀመረ፡፡ ከደጅ “ከብቶችህ ማሳዬ ውስጥ ገቡ!”
የሚል የጎረቤት ጩኸት ሰምቶ በሬዎቹን ሊያስገባ እንደሚወጣ ሲናገር ሚስቱ “እሱን ለእኔ ተወው፡፡ እኔ አስገባቸዋለሁ፡፡” አለችው፡፡
ይህንን ብላ ሚስቱ ስትወጣ ሰው ሁሉ ተከተላት፡፡ ታዲያ እሱ ቁምጣውን አውልቆ እሳቱን መሞቅ ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ ከሩቅ ብልቱን ያየች ድመት አይጥ መስሏት ዘላ ነከሰችው፡፡ ድመቷም የሰውየውን ጩኸት ስትሰማ መጎተቷን ቀጠለች፡፡ እሱም ጩኸቱን አላቆመም፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚስቱ ወደቤት ስትመለስ ሁኔታውን አይታ በፍጥነት ትልቅ ዱላ አንስታ የድመቷን መሃል ወገብ ብትላት ድመቷ ሞተች፤ ሰውየውም ተረፈ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|