የኃይለሥላሴ ምህረት
በወርቁ መርሻ የተተረከ
ሞጣ ከምትባል አንዲት መንደር ውስጥ የሚኖር ሰው ነበር፡፡ ሰውየውም ያለምንም ምክንያት “አንድ ቀን ንጉስ እሆናለሁ! አንድ ቀን ንጉሥ እሆናለሁ!” እያለ ደጋግሞ ይናገር ነበር፡፡
በዚህም ምክንያት ወደ ንጉሡ ዘንድ ለፍርድ ቀረበ፡፡ ንጉሡም “ይህንን ሰው ለምንድነው ያመጣችሁት?” ብለው በጠየቁ ጊዜ ሰዎቹም “ምንም ንጉሣዊ ደም ሳይኖረው አንድ ቀን ንጉሥ እንደሚሆን ይናገራል፡፡” ብለው ከሰሱት፡፡
ንጉሡም “ህዝቡን ሰብስቦ ነው ይህንን የተናገረው? ቅስቀሣስ አድርጓል?” ብለው ሲጠይቁ ሰዎቹ “አላደረገም::” ብለው መለሱ፡፡ “በሉ ልቀቁት” አሉ ኃይለሥላሴ “የሰውን ምኞት መግታት አይቻልም፡፡”
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|