አሁንም እብድ
በሽመላሽ በቀለ የተተረከ
በአንድ ወቅት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው አማኑኤል ሆስፒታል ውስጥ የሚታከም እብድ ሰው ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ሰው ከሆስፒታል መውጣት ፈልጎ ዶክተሩ ጋ በመሄድ ደህንነቱን ይነግረዋል፡፡
“አሁን ከአእምሮ ችግሬ ድኛለሁ፡፡”
ዶክተሩም ያበዱ ሰዎች ምንም ነገር ስለማያውቁ መዳን አለመዳኑን እንዴት እንዳወቀ ጠየቀው፡፡
እብዱም ሰው ወደ ጭንቅላቱ እየጠቆመ “ጥሩ ማሰቢያ ኩላሊት አለኝ፡፡” አለው፡፡
ዶክተሩም “በል አሁንም እብድ ነህ፡፡” አለው ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|