ጌታ ያድናል
በሽመላሽ በቀለ የተተረከ
በአገራችን አንድ እንዲህ የሚባል ትልቅ አባባል አለ “ጌታ እንኳን ከተወረወረ ቃል ከተወረወረ ጦርም ያድናል፡፡”
እናም ከእለታት አንድ ቀን አንዲት በጣም በጣም የተራበች ቀበሮ ጌታዋ የምትበላውን ነገር እንዲጥልላት ትፀልይ ነበር፡፡
አንድ በግ ደግሞ አንበሳ አይቶ ፈጣሪውን ከአንበሣው አፍ እንዲያድነው ይፀልይ ነበር፡፡ አንድ አህያ ደግሞ ፈጣሪውን ሣያይ ዝም ብሎ ተጋድሞ ነበር፡፡
ቀበሮውም አህያውን አይቶ ገደለው፡፡ አንበሣውም በጉን አይቶ በማሳደድ ላይ ሳለ ቀበሮው አህያውን መብላት ሲጀምር ይደርስበታል፡፡ ቀበሮውም አንበሣው እንዳይበላው ሲሸሽ አንበሣው አህያውን በላ፡፡ በዚህ አይነት በጉ ከሁለቱም አመለጠ፡፡
እናም አባባሉ እውነት ነው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|