በሪዎ ደላላ፣ እውነተኛ ታሪክ
በሽመላሽ በቀለ የተተረከ
በአገራችን አንድ አባ አዘነች እየተባሉ በሴት ስም የሚጠሩ መነኩሴ ነበሩ፡፡ አንድ ደግሞ ከሰማይ ከምድር የተጣለ አማፂ ጦረኛ ነበር፡፡
የአባይ ምንጭ በሆነው ሰቀላ ዳሞት ውስጥ የምትገኝ አረብ ገቤ የምትባል ሥፍራ ነበረች፡፡
እናም አንድ ቀን በገበያው መሃል በአንድ ዛፍ ላይ የተሰቀለ ሰው አይቶ የዚያች ወረዳ ገዢ አባ አዘነችን “ያ ዛፍ ላይ የተሰቀለው ሰው ማነው?” ብሎ ጠየቃቸው፡፡
አባ አዘነችም “ባሪዎ ደላላ ነው፡፡” ብለው መለሱለት፡፡
ገዢውም ልዑል ኃይሉ ተክለሃይማኖት የሚባል ሲሆን ሰውየውን የሞት ፍርድ የፈረደበት ራሱ ነበርና እንዲህ አለ “አይ ባሪዎ ደላላ! ከሰማይም ከምድርም ተጣልተህ በገነትና በምድር መሃከል በዛፍ ላይ ትቀር!”
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|