የአብዮት በዓል
በሽመላሽ በቀለ የተተረከ
በደርግደርግ የኃይለ ሥላሴን መንግስት ገልብጦ እስከ 1983 ዓ.ም በስልጣን ላይ የቆየ የኮሚኒስት አመራር ነው፡፡ ጊዜ የቡዊ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበረ አንድ ቆምጨ አምባው የተባለ ሰው ነበር፡፡ አራተኛውን የአብዮት በዓል 40 ሻማ አብርቶ በማክበር ይታወቃል፡፡ በኋላም ከቡዊ ወደ መተከል ተዛውሮ በመሥራት ላይ ሣለ አንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ቆምጨ አምባውን የዓመት ፈቃድ እንዲሰጠው ይጠይቀዋል፡፡
ቆምጨ አምባውም የዓመት እረፍት መውሰድ የመምህሩ መብት መሆኑን ዘንግቶ ፈቃዱን ለማግኘት አንድ ጥያቄ መመለስ እንዳለበት ይነግረዋል፡፡
”አራተኛውን የአብዮት በዓል 40 ሻማ አብርቶ ያከበረው ማነው?” ብሎ ሲጠይቀው መምህሩም “ይህማ ቀላል ነው:: ያ ሰው ታላቁ ጓድ ቆምጨ አምባው ነው፡፡” ብሎ ሲመልስለት ቆምጨ አምባውም ያለምንም ህጋዊ ማስረጃ የስድስት ወር ፈቃድ ሰጠው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|