ብር ልጄ
በዳንኤል ለገሠ የተተረከ
አንድ አለቃ ገብረሃና የተባሉ ሰው ነበሩ፡፡ እኝህ ሰው ታዲያ አንድ ቀን ገንዘባቸውን ሁሉ ሰብስበው አዲስ አበባን ትተው ወደ ጎጃምየቀድሞ የኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብ ጠቅላይ ግዛት፡፡ ለመሄድ ፈለጉ፡፡ ገንዘባቸውም እጅግ ብዙ ስለነበረ በከረጢት ተሸክመውት ሄዱ፡፡
አባይ ድልድይ እንደደረሱም ፖሊሶች ገንዘባቸውን እንዳይወስዱባቸው ፈርተው እንዴት ሊያሸሹት እንደሚችሉ ሲያስቡ ቆዩና በመጨረሻም አንድ ሃሣብ መጣላቸው፡፡ ብልሃቱም ገንዘባቸውን በአስከሬን ሣጥን ውስጥ ከተው ልጃቸው እንደሞተባቸው ማስመሰል ነበር፡፡
እናም ገንዘቡን ሳጥን ውስጥ ከተው “ብርብር የኢትዮጵያ ዋና የመገበያያ ገንዘብ ነው፡፡ (ፖሊሶቹ ብር የልጁ ስም መስሏቸው ተሞኙ፡፡) ልጄ! ብር ልጄ!” እያሉ ያለቅሱ ጀመር፡፡ ፖሊሶቹም እውነትም ልጅ የሞተባቸው ስለመሰላቸው አብረው አልቅሰው ሳጥኑን ሳይፈትሹ አሳለፏቸው፡፡
የፍተሻውንም ቦታ እንዳለፉ “ጅል ፖሊሶች፣ በቀላሉ አሞኘኋቸው” አሉ ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|