የእራት ወጥ
በዳንኤል ለገሠ የተተረከ
በአንድ ወቅት አንድ አለቃ ገብረሃና የተባሉ ሰው ነበሩ፡፡ ሚስታቸውም ወ/ሮወ/ሮ በአማርኛ የአንድ ያገባች ሴት መጠሪያ ሲሆን በኢትዮጵያ ሚስቶች የባላቸውን መጠሪያ ስም አይወርሱም፡፡ ማዘንጊያሽ ይባሉ ነበር፡፡ ታዲያ አንድ ቀን ማዘንጊያሽ ለእራታቸው የሚሆን ወጥ በማብሰል ላይ ሳሉ ባለቤታቸው አብረዋቸው ቁጭ ብለው የእራቱን መድረስ ይጠባበቁ ነበር፡፡ ሚስታቸውም ወጡ መብሰል አለመብሰሉን አሁንም አሁንም በማማሰያ እየቀመሱ ይፈትሹ ነበር፡፡ ይህንን ያዩት አለቃ በጣም ይበሣጩና “ማዘንጊያሽ ይህ እራታችን ከሆነ እኔም እቃዬን ይዤ ልምጣ?” አሏቸው ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|