ቆምጬ አምባውና ኳስ ሜዳው
በዳንኤል ገሠሠ የተተረከ
በአንድ ወቅት በአብዮቱ ጊዜ አንድ አቶአቶ በአማርኛ የወንድ መጠሪያ ነው፡፡ ቆምጨ አምባው የሚባል ሰው ነበር፡፡ እናም አንድ ትልቅ የእግር ኳስ ሜዳ አሰርቶ ለምርቃቱ ብዙ ሰዎች ይጠራል፡፡ ለምርቃቱ ከተጋበዙት ሰዎች አንድ ከአዲስ አበባ የመጣ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣን ነበር፡፡
ቆምጨ አምባውም እንዲህ ሲል የመክፈቻ ንግግር አደረገ፡፡
“የተወደዳችሁ እንግዶች! የእግር ኳስ ሜዳው በእበትየከብቶች እበት አንዳንድ ጊዜ ለቤት ወለል መለቅለቂያ ይውላል፡፡ ሳይለቀለቅ በመምጣታችሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡”
ሰው ሁሉ ሳቀ፡፡
ከዚያም በሁለት የእግር ኳስ ቡድኖች መሃከል ግጥሚያ ተካሄደ፡፡ ከአዲስ አበባ የመጣውም ሰው በመሣቅ “እኝህ ሁሉ ሰዎች ለምንድነው በአንድ ኳስ ብቻ የሚጫወቱት?” ብሎ ጠየቀ፡፡
ቆምጨ አምባውም “እኛ ገና በኢኮኖሚ ያደግን ስላልሆንን አገራችን ወደፊት ስትበለፅግ ለእያንዳንዱ ተጫዋች አንድ አንድ ኳስ እሰጣለሁ፡፡” አለ ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|