ልጅ እናቷን ምጥ አስተማረች
በዳንኤል ገሠሠ የተተረከ
በአንድ ወቅት ወ/ሮወ/ሮ የአንዲት ያገባች ሴት መጠሪያ ነው፡፡ አበራሽ የተባሉ ሶስት ልጆች ያሏቸው ሴት ነበሩ፡፡ ከሶስቱም ልጆቻቸው አንዷ ሴት ነበረች፡፡ ታዲያ አንድ ቀን እናት ከሴት ልጃቸው ጋር ብቻቸውን ቤታቸው ሳሉ በድንገት ምጥ ይይዛቸውና “አ..አ..አ..! ሰው ጥሪ! አ..አ..! ሰው ጥሪልኝ ልጄ፡፡” ማለት ይጀምራሉ፡፡
ልጃቸው አለሚቱም በሥጋት ተውጣ “እባክሽ እማማ በጀርባሽ ተኝተሽ ለማማጥ ሞክሪ፡፡ እማማ እባክሽ በጀርባሽ ተኝና እህህህ.. እያልሽ እምጪ፡፡” አለቻቸው፡፡
አለሚቱ ልጅ ስላልወለደች ምንም የወሊድ ልምድ አልነበራትም፡፡ እውቀት ሳይኖር ደግሞ ምንም ነገር ማስተማር አይቻልም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ታዲያ አንድ ጎረቤታቸው ሁኔታውን ስለሰማች ሮጣ መጣች፡፡ ሴትየዋም “ሰው ጥሪልኝ ሲሉሽ ለምን አልተጣራሽም?” ብላ አለሚቱን ብትጠይቃት አለሚቱ መልስ ሳትሰጣት ዝም አለች፡፡ ሆኖም ምጥ ላይ የነበሩ እናቷ “ተያት ምጥ እስተማረችኝ ነው፡፡” ብለው መለሱ፡፡
ጎረቤትየዋም በአስቸኳይ በአቅራቢያው ወደሚገኘው ክሊኒክ ወሰደቻቸው፡፡ ታሪኩም “ልጅ እናቷን ምጥ አስተማረች” ተብሎ ቀረ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|