ሁለቱ ፍቅረኛሞች
በሺመላሽ በቀለ የተተረከ
በባህር ዳር አካባቢ የሚነገር አንድ ታሪክ አለ፡፡
በአንድ ወቅት ሁለት ፍቅረኛሞች ጣና ሃይቅጣና በኢትዮጵያ ትልቁ ሃይቅ ሲሆን የአባይ ወንዝ መነሻም ነው፡፡ የሚገኘውም በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ነው፡፡ ላይ ወደሚገኙት ገዳማት ይሄዳሉ፡፡ የአንዱ ገዳም ስም ደጋ እስጢፋኖስ ይባላል፡፡
ወደዚህም ገዳም በታንኳ ሄዱ፡፡ ከገዳሙ እንደደረሱም ታንኳቸውን ሃይቁ ዳር ትተው በገዳሙ ውስጥ ጥሩ የፍቅር ጊዜ ማሳለፍ ጀመሩ፡፡
በዚህን ጊዜ ታዲያ ታንኳቸው በማዕበል በመወሰዷ እነርሱም አብረው ጠፍተዋል በሚል ሰዎች ይፈልጓቸው ጀመር፡፡ ስለፍቅረኛሞቹ መጥፋት በከተማው ዙሪያ ብዙ ነገር ተባለ፡፡ አንድ የከተማው ሰው ስለእነርሱ ብዙ ያውቅ ነበርና ይፈልጋቸው ጀመር፡፡ ወደ ተባለውም ገዳም በመሄድ ሊያገኛቸው ሞከረ፡፡ ልብሳቸውንም ከሩቅ አይቶ ደነገጠ፡፡ እየሮጠም ወደእነርሱ ሲደርስ አብረው ተኝተው ግን ሞተው አገኛቸው፡፡
በዚህም ምክንያት ገዳሙ አሁን የፍቅር ጠርዝ እየተባለ ይጠራል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|