እንኳን ከኳስ ከጥፋትም
በዳንኤል ገሠሠ የተተረከ
ከዕለታት አንድ ቀን አፄ ኃይለሥላሴና የኬንያው ፕሬዝደንት ጆሞ ኬንያታ የአገሮቻቸው ብሔራዊ ቡድኖች የእግር ኳስ ግጥሚያ ሲያደርጉ ይመለከቱ ነበር፡፡ ታዲያ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ጨዋታው ይጠናቀቃል፡፡ በመጨረሻም የጨዋታው ዳኛ ሁለቱ መሪዎች እንደ ግብ ጠባቂ ሆነው ጨዋታው ይዳኛል ብለው ወሰኑ፡፡
በዚህም መሠረት በመጀመሪያ ጆሞ ኬንያታ ግብ ጠባቂ ሆነው የኢትዮጵያው ንጉስ ፍፁም ቅጣት ምት በመምታት ጎል አስቆጠሩ፡፡
ቀጥሎ ፍፁም ቅጣት ምት መምታቱ የኬንያው ፕሬዝደንት ተራ ስለነበር የኢትዮጵያው ንጉሥ ጎል ጠባቂ ሆኑ፡፡
እናም የኬንያው መሪ ኳሱን ለመምታት ከሌላኛው የግብ ክልል ተነስተው ሜዳውን ሙሉ ሲንደረደሩ ባዩ ጊዜ የኢትዮጵያው ንጉሥ ግቡን ትተው ስለሸሹ የኬንያው መሪ ግብ ያስቆጥራሉ፡፡
ኃይለሥላሴም “ለምንድነው የሸሹት?” ተብለው ሲጠየቁ “እኛ ኢትዮጵያውያን እንኳን ከኳስ ከጥይትም እናመልጣለን፡፡” ብለው መለሱ ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|