ስስታሙ አባ ሃና
በወርቁ መርሻ የተተረከ
የአፄ ኃይለሥላሴ ባለቤት የነበሩት እቴጌ መነን በገነት ውስጥ ሲኖሩ የንጉሡ ግምጃ ቤት ኃላፊ የነበሩት አባ ሃናአባ ሃና የኃይለሥላሴ ንስሃ አባት የነበረ ታሪካዊ ባህታዊ ሰው ነበሩ፡፡ የተባሉ ስስታም ሰው በሲኦል ይኖሩ ነበር ተብሎ ይታመናል፡፡
ታዲያ አንድ ቀን አባ ሃና ወደ ገነት ሄደው እቴጌ መነንን ለመጎብኘት ጠይቀው ይፈቀድላቸዋል፡፡ ከገነትም እንደደረሱ እቴጌ መነንን ሲያይዋቸው በደስታ ዘለው ይጠመጠሙባቸዋል፡፡ በገነትም ትንሽ እንደቆዩ ወደ ሲኦል እንዲመለሱ ቢጠሩ አሻፈረኝ ይላሉ፡፡
ታዲያ በመጨረሻ ጉዳዩ ለገነት አስተዳዳሪ ሲነገረው “እሱም ችግር የለም:: ይህ ሰው ስስታም ሰው እንደሆነ አውቃለሁ፡፡” አላቸው፡፡
ከዚያም ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ገነት መግቢያ ሄዶ “ይህ ገንዘብ የማነው?” ብሎ ጮኸ፡፡
አባ ሃናም በፍጥነት “የእኔ ነው፡፡” ብሎ ሮጦ ወጣ፡፡ በዚህም ሁኔታ ጥቂት ሣንቲሞች ለማግኘት ሲል ገነትን አጣ ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|