አለቃ ገብረሃና እና መድኃኒት አዋቂው ሰው
በያለምጌታ ማሞ የተተረከ
በአንድ ወቅት በጣም ታዋቂና ብልህ የነበሩት አለቃ ገብረሃና ሰውነታቸው ቆስሎ ይታመማሉ፡፡ ታዲያ ወደ አንድ የባህል መድኃኒት አዋቂ ሰው ዘንድ ሄደው ቢጠይቁ ሰውየውም መድኃኑቱ በጣም ከባድ ስለሆነ እንደማይችሉት ይነግሯቸዋል፡፡
“አለቃም ሁልጊዜ ከምሰቃይ አንድ ቀን ብጨነቅ ይሻለኛል፡፡” ብለው መድኃኒቱን ለመውሰድ ወሰኑ፡፡
እናም መድኃኒት አዋቂው ሰው የሰላ ብረት በእሳት አግሎ ብረቱ ፍም ሲመስል ቁስሉ ላይ አኖረው፡፡
ታዲያ ቁስሉ ፊንጢጣቸው ላይ ስለነበር አለቃ ዓይነምድራቸው እንዳመለጣቸው አይቶ ሰውየው “ምነው አለቃ እየቀዘኑ እኮ ነው!?” ቢላቸው አለቃም ቀበል ብለው “ምን ማለትህ ’¨<; ቤት ሲቃጠል ዕቃውን ማሸሽ ይገባ የለም እንዴ;” አሉት ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|