እናት ጦጣ እና አባት ዝንጀሮ
በይርጋ እጅጉ የተተረከ
በአንድ ወቅት አንዲት ጦጣ እና አንዲት ዝንጀሮ ተጋብተው ለረጅም ጊዜ አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ አብረው እየኖሩም ሳለ አንድ ጊዜ ክፉ ረሃብ ይገጥማቸውና መንደራቸውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታ ይሰደዳሉ፡፡ እማ ጦጤእማ ጦጤ= እናት ጦጣ ልጆቿን ሁሉ ይዛ ተሰደደች፡፡ በመንገዳቸውም እየሄዱ ሳለ እማ ጦጤ ላባ ስታገኝ አባ ዝንጀሮአባ ዝንጀሮ= አባት ዝንጀሮ የሰላ ቢላዋ አገኘ፡፡ እማ ጦጤም ለአባ ዝንጀሮ እንዲህ አለችው “ተመልከት የእኔ መተጣጠፍ ይችላል:: ያንተ ግን አይችልም፡፡” እሱም “እንለዋወጥ” ብሏት ካሳመነችው በኋላ እሱ ላባውን ሲወስድ እሷ ቢላዋውን ወሰደች፡፡
ከዚያም እየተጓዙ ሳለ በመንገዳቸው ላይ አንድ አህያና አንድ ላም አገኙ፡፡ ጦጢት አህያውን ስትወስድ ዝንጀሮው ላሟን ወሰደ፡፡ ነገር ግን ጦጣዋ እርቧት ስለነበር አህያውን በላሟ መለወጥ ፈለገች፡፡ ስለዚህ አህያውን ስትደበድበው ከቆዳው ላይ አቧራ ይነሳ ጀመር፡፡
እሷም “ተመልከት! ይህ አቧራ አህያው ወፍራም መሆኑን ያሳያል፡፡ ያንተ ላም ግን ከሲታ ናት፡፡ መትተሃትም ማየት ትችላለህ፡፡? አለችው፡፡ ዝንጀሮውም ላሚቷን ቢመታት ምንም ነገር ስላጣ ወፍራሙን አህያ ሊወስደው ፈለገ፡፡ “እንለዋወጥ ያንቺን ስጭኝና የእኔን ውሰጂ!” ብሎ ጮሆባት በመጨረሻም በግድ አህያውን ወሰደ፡፡ ከዚህ በኋላ ዝንጀሮውና ጦጣዋ መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡ እየተጓዙም እያለ ሁለት ጎጆዎችን አገኙ፡፡ አንደኛው ጎጆ ዘጠኝ ቀዳዳዎች ያሉት ሲሆን ይህንንም ጦጣዋ ወሰደችው፡፡ ዝንጀሮው ሌላኛውንና ምንም ቀዳዳዎች የሌሉትን በደንብ የተሰራ ጎጆ ወሰደ፡፡ ሁለቱም ላማቸውንና አህያቸውን ይዘው ወደየጎጆአቸው ገቡ፡፡ ጦጣዋም እንዲህ አለች “አየህ! የእኔ ጎጆ ዘጠኝ ቀዳዳዎች አሉት፡፡ ማታ አያ ጅቦ በአንዱ ቀዳዳ ቢመጣብኝ እንኳ በሌላኛው አመልጣለሁ፡፡ ያንተ ጎጆ ግን ምንም ማምለጫ የለውም፡፡”
“ማታ አያ ጅቦ ቢመጣብኝ ምን አደርጋለሁ?”
አዎ ትክክል ነህ እንቀያየር
በዚህም ተስማምተው ተቀያየሩ
ማታውንም አያ ጅቦ መጥቶ የዝንጀሮ ጎጆ ውስጥ ገባ አህያውንም እንደያዘው ዝንጀሮው በአንዱ ቀዳዳ አምልጦ ወጥቶ የጦጣዋ ጎጆ ጣሪያ ላይ ተደበቀ፡፡
ዝናቡም በመጣ ጊዜ ዝንጀሮው በጣም ተቸገረ፡፡ በዚህም ጊዜ ጦጣዋ ላሚቷን አርዳ ከልጆቿ ጋር በጎጆዋ ውስጥ እየበላች ነበር፡፡ በሌላው ጎጆ ውስጥ ደግሞ ጅቦቹ “ሃ!ሃ!ሃ!” ብለው እየሳቁ አህያዋን ይመገቡ ነበር፡፡
በነጋ ጊዜም ጦጣዋ ትጨነቅ ጀመር፡፡ “አሁን ምን ብዬ ነው ለዝንጀሮው የምነግረው? እንዳታለልኩት ስለሚያውቅ አንገቴ ላይ ቆሞ አንቆ ነው የሚገድለኝ፡፡”
ከዚያም አንድ ሃሳብ መጣላት፡፡ ዝንጀሮው ከጣሪያ ወርዶ እስኪመጣ ድረስ አንድ ድቡልቡል ድንጋይ በእሳት አጋለች፡፡ የጋለውንም ድንጋይ በስጋ ሸፍና አዘጋጀች፡፡
“የአምላክ ያለህ!” ብላ በመጮህ ልቧን ትደቃ ጀመር፡፡ “በጣም ታሳዝናለህ! ምግብ አዘጋጅቼልሃለው::” ስትለው አፉን በከፈተ ጊዜ በስጋ የተጠቀለለውን የጋለ ድንጋይ አፉ ውስጥ ስትከትበት ወዲያው ሞተ፡፡
ወዲያውም የቀረውን ስጋ ከልጆቿ ጋር ተመግባ የሞተውን ዝንጀሮ አስከሬን ከቤቷ ኋላ ›ekSÖችው፡፡
በሶስተኛው ቀንም ነብር ወደሷ መጣ፡፡ ነብሩንም ባየችው ጊዜ በጣም ፈርታ ነበር፡፡ እሱም እንዲህ አላት “አያ ጦጢት እዚህ አካባቢ ብዙ ፍየሎች ስላሉ ከሁሉ ትልቁን ይዘሽልኝ ነይ!” ብሎ አዘዛት፡፡ እሷም “አያ ነብር ምንም አያሳስብህ:: በጣም ትልቁን ፍየል አመጣልሃለው፡፡ ነገር ግን ትልቁ ፍየል አንተን ባየ ጊዜ ስለሚሸሽ ልይዘው አልችልም፡፡ ስለዚህ ምን ባደርግ ይሻለኛል? ፊትህን አዙረህ ጀርባህን ብታሳየው ጭራህን ከፍየሉ ጭራ ጋር አስረውና አንተም ፍየሉን በጭራህ እየጎተትክ ወደ ዋሻህ ትመለሳለህ፡፡” አለች፡፡
ነብሩም በዚህ ተስማማ፡፡ እሷም ወደ ቤቷ ኋላ ይዛው ሄዳ ፊትህን አዙር አለችውና ጭራውን ከሞተው ዝንጀሮ ጭራ ጋር ቋጥራው አሁን በል እሩጥ አለችው፡፡ ነብሩም የሞተውን ዝንጀሮ እየጎተተ ወደ ዋሻው ሄደ፡፡ እዚያም እንደደረሰ ዞር ብሎ ሲያይ ዝንጀሮውን አየ፡፡ የዝንጀሮውም አፍ ተከፍቶና ሰውነቱ አብጦ ነበር፡፡ ነብሩ ባየው ጊዜ ደንግጦ “ምን አይነት ትልቅ እንስሳ ነው?” በማለት ወደ ጫካው ተመልሶ ሲሸሽ ከተራራው ላይ የወዳደቁ ድንጋዮች ደብድበው ገደሉት፡፡
ከዚህም በኋላ ጦጣዋና ልጆቿ በሰላም አብረው መኖር ጀመሩ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|