የጅቦች ሃዘን
በይርጋ እጅጉ የተተረከ
በአንድ ወቅት አንድ የጅቦች ልጅ ሞቶ ጅቦች ሁሉ ሃዘን ተቀምጠው ነበር፡፡ ይህም ዜና ከአህዮች ጆሮ ደርሶ ነበርና አንድ አህያ እንዲህ አለ “ለምን ለቅሶ አንደርሳቸውም? ይህንንም ካደረግን እኛን ማደን ይተዋሉ፡፡”
ሌሎቹም እንዲህ አሉ “ከጅቦቹ ጋር ወዳጅነት ለመመስረት ይህ መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ ስለዚህ እንሂድ::” ብለው ተስማምተው ወደ ጅቡ ቤት አቀኑ፡፡
ጅቦቹም አህዮቹን በሩቅ ባዩ ጊዜ “እነዚያ ወደእኛ የሚመጡት እንስሳት እነማን ናቸው?” ብለው ጠየቁ፡፡ ሁሉም በመገረም እያዩአቸው ሳለ አህዮቹ በቀጥታ ወደ ጅቡ ቤት ገቡ፡፡ ያህዮቹም መሪ እንዲህ አለ “የምትበሉት ነገር ጥቁር እንኳን ቢሆን የጅብ ፋንድያ ነጭ ነው፡፡ የጌታዬን ልጅ ምን አገኘው?” ጅቡም እንዲህ ብሎ መለሰ “ምንም ብትለኝ አይገባኝም፡፡ አሁን ጅቦቹ ሁሉ ተርበዋልና ምን ይበላሉ?”
አህዮቹም ሁሉ በጭንቀት እርስ በእርስ መተያየት ጀመሩ፡፡ አንደኛውም “ብናመልጥ ይሻላል” ብሎ በለሆሳስ ተናገረ፡፡ “ሌላኛው ግን አሁንማ በእጃቸው ውስጥ ነው ያለነው፡፡” አለ፡፡
“ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻለናል?”
“ከንፈራችንን እንስጣቸውና ያንን ይብሉ::”
በዚህም ተስማምተው አለቃቸው ይህንኑ ለጅቦቹ አስረዳ ጅቦቹም በሙሉ ወደ እህዮቹ ዘለው ከንፈሮቻቸውን በጭቀው ጥለው በሁለት ጎራ ተፋጠጡ፡፡
ስለዚህ አህዮቹ ከንፈር ስለሌላቸው በጅቦቹ የሚስቁ ይመስል ስለነበር አንዱ ጅብ “ልጃችን ሞቶ እያለ እንዴት ነው የምትስቁብን? ልታሾፉብን ነው የመጣችሁት? አለ፡፡
በዚህም ጊዜ ጅቦቹ በሙሉ ዘለው አህዮቹን ይዘው በሏቸው፡፡
ከዚያን ጊዜ አንስቶ አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ ይባል ጀመር፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|