የምድሪቷ ፍሬ
በወርቁ መርሻ የተተረከ
የጎጃምጎጃም የቀድሞ የሰሜን ምእራብ ኢትዮጵያ ግዛት ነው፡፡ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ደብረ ማርቆስ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ አንድ ቀኝቀኝ አዝማች ማለት የጦር ሃይሉ የቀኝ ክንፍ አዛዥ መጠሪያ ነው፡፡ አዝማች ሰውነቴ የተባሉ ሰው ነበሩ፡፡ እሳቸውም ጠጅጠጅ ከማር የሚጠመቅ የአልኮል መጠጥ ነው፡፡ በጣም ይወዱ ነበርና እርስታቸውን ሸጡ፡፡
መሬታቸውን ለምን እንደሸጡ በተጠየቁም ጊዜ “ምድሪቷ ሳትበላኝ በፊት የምድሪቷን ፍሬ ልብላ ብዬ ነው፡፡” ብለው መለሱ፡፡
ባህርዛፉንምከ1881-1985 ድረስ ኢትዮጵያን የገዙት አፄ ምኒሊክ ወደ 19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ባህርዛፍን ከአውስትራሊያ ወደ ኢትዮጵያ አስገቡ፡፡ ፈጥኖ ማደጉ፣ ለማገዶነትና ለግንባታ አመቺ መሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት እንዲዳረስ አድርጎታል፡፡ በለጋነቱ ሸጡት፡፡ አሁንም ለምን እንዲህ እንዳደረጉ ሲጠየቁ “እሱ እየወፈረ እኔ መክሳት አልፈልግም፡፡” ብለው መለሱ ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|