ጥቁሩ ቁራ
በፕሮፌሰር አህመድ መሃመድ ዓሊ የተተረከ
ቁራ በአንድ ወቅት ሼኪ ወይም ቄስ ስለነበረ ቀለሙም ነጭ ነበር፡፡ ነገር ግን ሌሎቹ አእዋፋት ሁሉ አቤቱታ አሰሙበት፡፡ እንደዚህም አሉ “በአንድ ወገን ሥጋ ይበላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ፍራፍሬ ይበላል፡፡”
ከዚያም ሁሉም አእዋፋት ተሰባስበው “አንተ ሼኪ ወይም ቄስ ነህ! ነገር ግን የምትሰራው ነገር ስህተት ነው፡፡ ትንንሾቹ አእዋፋት ሥጋ መመገብ አለባቸው፡፡ ትልልቆቹ ደግሞ ፍራፍሬ ይብሉ፡፡ አንተ ግን ከሁለቱም ወገን ትበላለህ፡፡” አሉት፡፡
በሱማሌ ብቻ ሳይሆን በኩሽ ባህል በአጠቃላይ ቁራ የፀሃይ አምላክ የሆነው የዋቅ ተወካይ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ኦሮሞዎችም ጭምር በፀሃይ አምላክ ያምናሉ፡፡ ቁራ የፀሃይ አምላክ ዋቅ የተናገረውን ለሰዎች የሚተረጉምና የሰዎችንም መልዕክት ወደ ፀሃዩ አምላክ የሚያደርስ መሆኑን ያምናሉ፡፡
ቁራውም ሲናገር “ዋቅ! ዋቅ!” እያለ ነው፡፡
ሆኖም ቁራው እምነት በማጉደል ሁለቱንም ነገሮች ማለትም ፍራፍሬና ሥጋ ስለበላ ቅጣት ተጣለበት፡፡ ረግመውትም ጥቁር ሆኖ ቀረ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|